የኢንጋቢሬ ችሎት
ሐሙስ፣ ጳጉሜን 1 2004የሩዋንዳ ከፍተኛ ፍርድ ቤት በሩዋንዳ ከአሸባሪዎች ጋር በማበር ና በሌሎችም ወንጀሎች ክስ በተመሰረተባቸው ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ቪክቷር ኢንጋቢሬ ላይ ነገ የመጨረሻ ውሳኔ ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል ። ኢንጋቢሪ የዘር ልዩነት በስፋት በመቀስቀስ እና እጎአ በ1994 በሩዋንዳ የተካሄደውን የዘር ማጥፋት ወንጀል በመካድም ተከሰዋል ። ደጋፊዎቻቸው ክሱ ፖለቲካዊ አላማ ያለው ነው ይላሉ ። የዶቼቬለው
ቪክቷር ኢንጋቢሬ ከተሰደዱበት ከኔዘርላንድስ ወደ ሃገራቸው የተመለሱት እጎአ በ 2010 አም ነበር ። ያኔ ወደ ሃገራቸው የገቡትም የተባበሩት ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በምሃፃሩ FDU Inkingi የተባለውን ተቃዋሚ ፓርቲያቸውን ለማስመዝገብ ና በፕሬዝዳንታዊ ምርጫም ለመካፈል ነበር ። ይሁንና በዚያው አመት በመስከረም ወር ለሚካሄደው ምርጫ ፓርቲያቸውን ለማስመዝገብ ያደረጉት ሙከራ አልተሳካም ። ይልቁንም ኢንጋቢሬ በአሸባሪነት የተፈረጀውን የሩዋንዳ ነፃ አውጭ ዲሞክራሲያዊ ኃይሎች በምህፃሩ FDRL የተባለውን ቡድን በገንዘብ ደግፈዋል ፣ የዘር ልዩነት ለማስፋፋት ቀስቅሰዋል እንዲሁም የሩዋንዳውን የዘር ማጥፋት ክደዋል ተብለው በቁም እስር እንዲቆዩ ተደረገ ። ኢንጊባራ በተለይ የዘር ማጥፋት ወንጀሎችን ክደዋል ተብለው የተከሰሱት ሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ በገቡበት እለት የዘር ማጥፋት ወንጀል ሰለባ ለሆኑ መታሰቢያ በተሰራው ማዕከል ተገኝተው ባሰሙት በዚህ ንግግር ምክንያት ነበር ።
« ሃገሪቱ ወደ ብሔራዊ እርቅ የሚያመራ ውጤታማ የፖለቲካ መርህ የላትም ። በዚህ የመታሰቢያ ማዕከል የቱትሲዎች የዘር ማጥፋት ወንጀል ብቻ ነው የታሰበው ። በሁቱ ህዝብ ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋም ማሰብ ይገባል ። እውነተኛ እርቅን ለማውረድ ከሁሉም በኩል ያለው መጥፎ ሁኔታ ግምት ውስጥ መግባት ይኖርበታል ። »
ኢንጋቢሬ FDRL ን በገንዘብ በመርዳት በቀረበባቸው ክስ የመሰከሩባቸው ሁለት የቀድሞው የቡድኑ አዛዦች ናቸው ። ሁለቱ አዛዦች ራሳቸው ተከሳሾች ናቸው ። የኢንጋቢሬ ጠበቃ 2 ቱ ሰዎች ጥፋተኝነታቸውን እንዳመኑ ተናግረው የመሰከሩትም ጥቅማቸውን ለማስጠበቅ ነው ብለዋል ። ባለፈው ሚያዚያ ጉዳይቸው በፍርድ ቤት በሚታይበት ወቅት ዳኞቹ አድሎ ይፈፅማሉ ስለኔም የምስክር ቃል ለመስጠት የተዘጋጀ ሰው ቃሉን እንዳይሰጥ ከልከለዋል ሲሉ ኢንጊጊባራ ችሎቱን አቋርጠው ወጥተው ነበር ። ብሪታኒያዊው ጠበቃቸው ኢያን ኤድዋርድስ ሁኔታውን ያብራራሉ
« በመርህ ደረጃ የያዙት አቋም ከአሁን በኋላ በችሎቱ ላይ መገኘት ለችሎቱ ክብር መስጠት ይሆናል ። በርካታ ችግሮች ቢኖሩም በሁሉም ችሎቶች ላይ በመገኘት ተባብረዋል ። ነገር ግን ይሄ የመጨረሻው በፍፁም ሊዋጥላቸው ያልቻለ ነገር ነው ። »
ተንታኞች እንደሚሉት የኢንጊባሬ ግጉዳይ ፖለቲካዊ አቅጣጫ ይዟል ። በነርሱ አስተያየት ክሶቹ በሩዋንዳ መንግሥትና በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም በ FDRL ና በ FDU Inkingi መካከል ከሚካሄደው ፖለቲካዊ ግጭት ጋር የተያያዘ ነው ። ዶክተር አሌክሳንደር ስትሮው በምሃፃሩ ጊጋ በሚባለው የአለም ዓቀፍ የአካባቢያዊ ጉዳዮች ጥናት ተቋም ባልደረባ ናቸው ። በርሳቸው አስተያየት ወሳኙ ጥያቄ ከኢንጊባሬ ክስ በስተጀርባ ያለው አላማ ምንድነው የሚለው ነው ።
« ተወደደም ተጠላም በሩዋንዳ ህግ ከ ዘር ማጥፋት አስተሳሰቦችና ቅስቀሳዎች እንዲሁም ልዩነቶችን ከማስፋፋት ጋር የተያያዙ ንግግሮች ሊያስቀጡ ይችላሉ ። ህጎቹን መተቸት ይቻላል ፤ ሆኖም ህጎቹ አሁንም ሩዋንዳ ውስጥ አንዳንድ ጉዳዮች ላይ እስተያየት እንዳይሰጥ የሚከለክሉ ናቸው ። ከተፈረደባቸው ፣ ዋናው ጥያቄ የክሱ አላማ ፖለቲካዊ ነው አይደለም የሚለው ነው ። »
የኢንጊባሪ ጠበቃ ክሱ ፖለቲካዊ መሆኑ አይጠራጥርም ነው የሚሉት ። ኢንጊባሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ የሩዋንዳ መንግሥት ብቸኛዋ ተቃዋሚ አይደሉም ። በልዩ ልዩ ምክንያቶች የታሰሩ ሌሎች ተቃዋሚዎችም አሉ ። ተቃዋሚዎችን የሚያስረው የሩዋንዳ መንግሥት ደግሞ ምሥራቅ ኮንጎ የሚንቀሳቀሱ አማፅያንን ይደግፋሉ ተብሎ በአንድ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዘገባ ተጋልጧል ። በዶክተር ስትሮህ እምነት ነገ በኢንጊቤሪ ላይ ከሚሰጠው ብይን ይልቅ የተባበሩት መንግሥታት በዚህ ዘገባ ላይ የሚያሳልፈው ውሳኔ በሩዋንዳ ላይ ይበልጥ ተፅእኖ ይኖረዋል ።
ሂሩት መለሰ
ተክሌ የኋላ