1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ውይይት፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካና የመገናኛ ብዙኃኑ አጣብቂኝ

እሑድ፣ የካቲት 4 2010

ባለፉት አመታት ኢትዮጵያ ያለፈችባቸው የፖለቲካ ውጥንቅጦች የመገናኛ ብዙኃኑን ሚና ቀይረውታል። በተለይ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልላዊ መንግሥቶች ቁጥጥር ሥር የሚገኙ የራዲዮ እና ቴሌቭዥን ጣቢያዎች ከወትሮው በተለየ ተቃውሞች ሲዘግቡ ታይቷል። ለውጡ ግን ለኢትዮጵያ መንግሥት ሹማምንት የሚዋጥ አይመስልም።

https://p.dw.com/p/2sTzK
Äthiopien Adama - Oromia TV headquarter
ምስል Tesfalem Waldyes

ውይይት፦የኢትዮጵያ ፖለቲካና የመገናኛ ብዙኃኑ አጣብቂኝ

የኢትዮጵያ የመንግሥት ኮምዩንኬሽን ጉዳዮች ፅሕፈት ቤት ኃላፊ ሚኒሥትሩ በቅርቡ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ "ግጭት ተባብሶ ቀጥሏል፣ ውጥረት ነግሷል" የሚሉ አሉታዊ ዘገባዎች ተበራክተዋል ሲሉ ተደምጠዋል። አዲስ አበባ ላይ በተካሔደ ውይይት የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን አብዛኞቹን መገናኛ ብዙኃን ወቅሷል። የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ መገናኛ ብዙኃኑ እንዴት ዘገቡት?  የመንግሥት ባለሥልጣናቱስ ትችት ምን ያክል ተገቢ ነው?

እሸቴ በቀለ
ማንተጋፍቶት ስለሺ