1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ መዉጣትና አጋጣሚዉ

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 28 2001

የጦሩ መዉጣት ከጉዳቱ ይልቅ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ጥሩ እድል ይፈጥራል

https://p.dw.com/p/GSzD
ከብሁዎቹ አማፂ ሐይላት ያንዱ ታጣቂምስል AP

የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቅቆ መዉጣቱ ለምሥራቅ አፍሪቃዊቱን ሐገር ፖለቲካዊ ቀዉስ ለማስወገድ ጥሩ አጋጣሚ ሊሆን እንደሚችል ጉዳዩን የሚከታተሉ የፖለቲካ አዋቂዎች አስታወቁ። ኢንተርናሽናል ክራይሲስ ግሩም የተሰኘዉ የፖለቲካ ጥናት ተቋም ባልደረቦች እንደሚሉት የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ መዉጣቱ የፀጥታ ክፍተት ማስከተሉ አይቀርም።ይሁንና አለም አቀፉ ማሕበረሰብ ካሰበበት የጦሩ መዉጣት ከጉዳቱ ይልቅ ፖለቲካዊ መፍትሔ ለማፈላለግ ጥሩ እድል ይፈጥራል።ነጋሽ መሐመድ የአጥኚዉ ተቋም የመርሕ ጉዳይ ምክትል ሐላፊ ዳኖልድ ስታይን በርግን አነጋግሮ የሚከተለዉን ዘገባ አጠናቅሯል።