1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጦርና ሶማሊያ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 17 2005

ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ብትወጣ የሚፈጠረው የፀጥታ ክፍተት ለአሸባብ አመቺ ሁኔታ መፍጠሩ እንደማይቀር ተናግረዋል ። ይሁንና ኢትዮጵያ ወታደሮቿ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጡ ብትናገርም ፣ ለራሷ የፀጥታ ጠቀሜታ ስትል እርምጃውን ትወስዳለች ተብሎ አይታሰብም ።

https://p.dw.com/p/18NTc
ምስል JENNY VAUGHAN/AFP/Getty Images

ኢትዮጵያ በቅርቡ እንዳስታወቀችው ወታደሮቿን ከሶማሊያ ካስወጣች በሶማሊያ ተጨማሪ የፀጥታ ችግር  ሊከሰት  እንደሚችል ተገለፀ ። በጉዳዩ ላይ ለዶቼቬለ አስተታየታታቸውን የሰጡት የምሥራቅ አፍሪቃ የፀጥታ ጉዳዮች ተመራማሪ አንድሪውስ አታ አሳሞዋ ኢትዮጵያ ከሶማሊያ ብትወጣ  የሚፈጠረው የፀጥታ ክፍተት ለአሸባብ አመቺ ሁኔታ መፍጠሩ እንደማይቀር ተናግረዋል ። ይሁንና ኢትዮጵያ ወታደሮቿ በቅርቡ ከሶማሊያ እንደሚወጡ ብትናገርም ፣ ለራሷ የፀጥታ ጠቀሜታ ስትል እርምጃውን ትወስዳለች ተብሎ አይታሰብም ።
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ከትንንት በስተያ ማክሰኞ ለህዝብ ተወካዮች ምክር  ባሰሙት ንግግር መንግሥታቸው ሶማሊያ የሚገኙትን ወታደሮች በሙሉ በቅርቡ እንደሚያስወጣ አስታውቀዋል ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት የኢትዮጵያ ወታደሮች አሁን በአፋጣኝ ሶማሊያን እየለቀቁ ወደ ድንበር አካባቢ እንዲሰፍሩ ይደረጋል ። ኢትዮጵያ እንዳለችው ይህን እርምጃ የምትወስድ ከሆነ ፕሪቶሪያ ደቡብ አፍሪቃ የሚገኘው የዓለም ዓቀፍ የፀጥታ ጥናት ተቋም ባልደረባ አንድሪውስ አታ አሳሞዋ  የሶማሊያ ፀጥታ መደፍረሱ አይቀርም ብለዋል ። አሳሞዋ ለዚህ አባባላቸውም አብነት ጠቅሰዋል  

Bildergalerie Somalia Sicherheitslage Kind und Soldat 2013
ምስል STUART PRICE/AFP/Getty Images


« ኢትዮጵያ ሰፋ ባሉ አካባቢዎች ጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር ታደርጋለች ። እንደሚመስለን የኢትዮጵያ ኃይሎች መውጣት በአፋጣኝ በአሸባብ ኃይሎች የሚሞላ የፀጥታ ክፍተት እንዲፈጠር ያደርጋል በቅርቡ የኢትዮጵያ ወታደሮች ባከል ከሚገኙ አንዳንድ አካባቢዎች ለቀው ሲወጡ አሸባብ   እነዚህን ቦታዎች መልሶ ለመያዝ ጊዜ አልፈጀበትም ። ምትክ ሳይገኝ ኢትዮጵያ ከያዘቻቸው አካባቢዎች ለቃየምትወጣ ከሆነ ፅጥታ እየደፈረሰ መሄዱን ማየታችን አይቀርም ። »
የኢትዮጵያ ወታደሮች ከሶማሊያ ሲወጡ እንደ አሳሞዋ የሚፈጠረው ችግር ይህ ብቻ አይደለም  ። ህዝቡም ለሌላ አደጋ መጋለጡ አይቀርም ።
« ፀጥታ መደፍረሱ ብቻ አይደለም አሸባብ በነዚህ አካባቢዎች የሚገኙ ህዝቦችን የኢትዮጵያ ወታደሮች በመደገፋቸው ምክንያት ለማንገላታትና ለማሰቃየት መሞከሩም አይቀርም ። ያ ማለት ወደፊት የሃገሪው ነዋሪዎች ሠላም እንዲሰፍንና ለፀጥታ ተብሎ ለማንናውም የውጭ ኃይል የሚሰጡትን ድጋፍም ዋጋ ያሳጣል ። ስለዚህ እስካሁን የተገኙትን ውጤቶች ፍሬ አልባ ሊያደርግ ስለሚችል ለዚህ እርምጃ አፋጣን ምላሽ መስጠቱ አስፈላጊ ነው ።»

Bildergalerie Somalia Sicherheitslage Marka 2012
ምስል Mohamed Abdiwahab/AFP/GettyImages

አቶ ኃይለ ማርያም እንዳሉት ኢትዮጵያ የሶማሊያ ዘመቻ ወጪዋን የምትሸፍነው ራሷ ናት ። ሶማሊያ ውስጥ ወታደሮቻቸውን በሶማሊያ ሠላም አስከባሪ ኃይል ስራ ያዘመቱ ሌሎች የአፍሪቃ ሃገራት ገንዘብ ሲከፈላቸው የኢትዮጵያ ሠራዊት ግን በዚህ  ውስጥ አልተካተተም ። ለኢትዮጵያ ቅሬታ ዋነኛው ምክንያት ሊሆን የሚችለው ይኽው የገንዘብ ጉዳይ ሳይሆን እንዳልቀረ ሮይተርስ ዲፕሎማቶችን ጠቅሶ ዘግቧል ። ሆኖም ኢትዮጵያ ወታደሮቿን  ከሶማሊያ አስወጣለሁ ብትልም ፣ ለራሷ የፀጥታ ጥቅም  ስትል ይህን እርምጃ ትወስዳለች ተብሎ አይገመትም ።  አሳሞዋ ግን ዘላቂው መፍትሄ ሶማሊያውያንን ብቁ ማድረግ ብቻ ነው ይላሉ ።  
« የሶማሊያ ፀጥታ በአስተማማኝነት እንዲቀጥል በሶማሊያዎች የሚመራ የፀጥታ ኃይል መገንባት አሁን ሶማሊያ የሚገኙትን የውጭ ኃይሎች የሚተካ ሠራዊት ማደራጀት ወሳኝ ነው ። አሁን መደረግ ያለበት ፣ መንግሥት በመላ ሃገሪቱ ፀጥታ ማስከበር እንዲችል ማብቃት ነው ። »

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ