1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ጉዳይ በአውሮጳ ፓርላማ

ሐሙስ፣ ኅዳር 1 2009

ትናንት ብራስልስ ቤልጂ,ም በሚገኘው የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን እንዲፈታ እና አዲስ ምርጫም እንዲጠራ ጥሪ ቀርቦለታል ።

https://p.dw.com/p/2SVNf
Brüssel Europäische Kommission Außenansicht
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

Beri.Brussels (Hearing on Ethiopia in EP) - MP3-Stereo

የኢትዮጵያን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት መንግሥት መሠረታዊ የለውጥ እርምጃዎችን እንዲወስድ ተጠየቀ ። ትናንት ብራስልስ ቤልጂ,ም በሚገኘው የአውሮጳ ህብረት ፓርላማ በተካሄደ ስብሰባ ላይ የኢትዮጵያ መንግሥት ያሰራቸውን እንዲፈታ እና አዲስ ምርጫም እንዲጠራ ጥሪ ቀርቦለታል ። በኢትዮጵያ ወቅታዊ ሁኔታ ላይ በተነጋገረው በዚሁ ስብሰባ ላይ ዶክተር መረራ ጉዲና የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ፕሬዝዳንት ፣ ዶክተር ብርሃኑ ነጋ የአርበኞች ግንቦት ሰባት መሪ እና አትሌት ፈይሳ ሌሊሳ ተገኝተው ንግግር አድርገዋል ። ስብሰባውን የጠሩት እና የመሩት ወይዘሮ አና ጎሜዥ የአውሮፓ ፓርላማ አባልና በፓርላማው የሰብዓዊ  መብቶች ንኡስ ኮሚቴ አባል  በስብሰባው ላይ የፓላማ አባላትና በርካታ ኢትዮጵያውያን ተሳትፈዋል።  ስብሰባውን የተከታተለው የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዘገባ አለው ።
ገበያው ንጉሴ 
ኂሩት መለሰ 
አዜብ ታደሰ