1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ የጨርቃጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች 

ሐሙስ፣ ግንቦት 1 2011

በመላው ዓለም ዝቅተኛ ክፍያ የሚያገኙት የኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካ ሠራተኞች መሆናቸውን አንድ የዩናይትድ ስቴትስ ተቋም አመለከተ። እንደተቋሙ በኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ፓርክ ለሚሠሩ ሠራተኞች የሚከፈለው ደሞዝ እጅግ ዝቅተኛ ነው።

https://p.dw.com/p/3IEsU
Äthiopien Textilindustrie
ምስል picture-alliance/dpa

ዝቅተኛ ገቢ እንደሚያገኙ ተገለጸ

 እንዲህ ያለ ክፍያ ያለበት ሌላ ሀገር በዓለም ላይ ፈልጎ ማግኘት አዳጋች ነው ሲሉ በዩናይትድ ስቴትስ የኒዉዮርክ ዩኒቨርሲቲ የተባለ የንግድ እና የሰብዓዊ መብቶች ማዕከል ምክትል ዳይሬክተር ለዶይቼ ቬለ DW ገልጸዋል። ርካሹን የሰው ጉልበት ተማምነው የልብሶቹ ፋብሪካዎች የሚስፋፉ ከሆነ የሰብዓዊ መብት ጥያቄን ስለሚያስነሳ አሳሳቢ መሆኑንም አመልክተዋል። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ልኮልናል።

መክብብ ሸዋ

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ