1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበርነት

ሰኞ፣ ጥር 13 2005

በ20ኛው የአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ መክፈቻ ላይም የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በአባል ሃገራት መሪዎች በይፋ እጎአ የ 2013 የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

https://p.dw.com/p/17OUQ
Ethiopian Prime Minster Hailemariam Desalegn (L) speaks during a meeting with his Somali counterpart Hassan Sheikh Mohamud (R- nicht im Bild - Anm. Bildredaktion) in Addis Ababa on November 28, 2012. Hailemariam reiterated Ethiopia?s commitment to keeping its troops in Somalia until African Union forces take over Ethiopian strongholds, but did not provide a timeline. Ethiopia sent troops and tanks into Somalia in November 2011 to support AU and Somali troops fighting Shebab extremists. They have since captured key towns from the Islamist militants, including Baidoa and Beledweyne. AFP PHOTO/JENNY VAUGHAN. (Photo credit should read JENNY VAUGHAN/AFP/Getty Images)
ምስል Getty Images

ኢትዮጵያ  በዙር የሚደርሰውን የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበርነት በቅርቡ ትረከባለች ተብሎ ይጠበቃል ። የፊታችን ኡህድ የሚጀመረው የአፍሪቃ ህብረት 20ኛው የመሪዎች ጉባኤ ኢትዮጵያን እጎአ የ2013 የአፍሪቃ ህብረት ሊቀመንበር አድርጎ እንደሚመርጥ ይጠበቃል ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ኢትዮጵያ ሃላፊነቱን ስትረከብ ከምታተኩርባቸው ጉዳዮች አንዱ የአፍሪቃ ሠላምና ፀጥታ ነው  ።

በሳምንቱ መጨረሻ ለሚካሄደው የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ የመነጋገሪያ አጀንዳ የሚያቀርቡት የአባል ሃገራት አምባሰደሮች ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ ጉባኤያቸውን ጀምረዋል ። ከአምባሰደሮቹ ቀጥሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በመጪው ሐሙስና አርብ ከተሰበሰቡ በኋላ የፊታችን እሁድና ሰኞ የአፍሪቃ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ይካሄዳል ። በዚህ በ20ኛው የአፍሪቃ ህብረት ጉባኤ መክፈቻ ላይም

African Union in Addis Abeba, Ethiopia Bild: Autor/Copyright: Getachew Tedla HAILEGIORGIS( Äthiopien DW Korri.)
አዲሱ የአፍሪቃ ህብረት ህንፃምስል DW

የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ በአባል ሃገራት መሪዎች በይፋ እጎአ የ 2013 የህብረቱ ሊቀመንበር ሆነው ይመረጣሉ ተብሎ ይጠበቃል ። የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ እንዳስታወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም የወቅቱ ሊቀመንበር የሚሆኑት ለምሥራቅ አፍሪቃ በዙር በደረሰው ተራ መሰረት ነው ።

በከዚህ ቀደሙ የዙር አሰራር መሠረት እስካሁን ተራው ለሰሜን ለደቡብ ለማዕከላዊ አፍሪቃ ና ለምዕራብ አፍሪቃ ደርሷል ። አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ የሊቀመንበርነት ሃላፊነቱን የሚረከቡት ከቤኒኑ ፕሬዝዳንት ከቦኒ ያያ ነው ። የአፍሪቃ ህብረት ከተመሰረተበት እጎአ ከ2003 ወዲህ  ኢትዮጵያ የህብረቱ ሊቀ መንበር ስትሆን የአሁኑ የመጀመሪያው ነው የሚሆነው ። ከምሥራቅ አፍሪቃ የመጨረሻዋ የህብረቱ ሊቀመንበር ታንዛኒያ ነበረች ። እጎአ በ 2009 የታንዛኒያው ፕሬዝዳንት ጃካያ ኪክዌቴ የህብረቱ ሊቀመንበር ነበሩ ።

Afrikanische Union Gebäude in Addis Abeba.jpg Foto: Maya Dreyer DW
የቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ህንፃምስል DW /Maya Dreyer

ኢትዮጵያ ይህን ሃላፊነት አሁን ማግኘቷ ድርጅቱን ለማጎልበት ጠንክራ እንድትሰራ እድል እንደሚሰጣት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ተናግረዋል ። አምባሳደሩ ኢትዮጵያ በሊቀ መንበርነቷ ዘመን ቅድሚያ የምትሰጣቸውን ዋና ዋና ጉዳዮችም ለዶቼቬለ ተናግረዋል ።የቀድሞው የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት ከተመሰረተ የፊታችን ግንቦት ግምሽ ምዕተ አመት ይደፍናል ። ድርጅቱ ወደ አፍሪቃ ህብረትነት ከተቀየረ ወዲህ ደግሞ ዘንድሮ የሚያካሂደው 20ኛውን የመሪዎች ጉባኤ ነው ። የአፍሪቃ አንድነት ድርጅት መሥራች ኢትዮጵያ ፣ የድርጅቱን የወርቅ ኢዮቤልዮ በአልና ና 20 ኛውን የመሪዎች ጉባኤም ድርጅቱ በተቋቋመባት በአዲስ አበባ ለማክበር በዝግጅት ላይ መሆኗን አምባሳደር ዲና ተናግረዋል ።

ሂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ