1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ የሰብአዊ መብት ይዞታና የአውሮፓ ፓርላማ

ሐሙስ፣ ጥር 16 2005

በኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዝ ላይ ያተኮረ ውይይት ትናንት ብራሰልስ ውስጥ በሚገኘው የአውሮፓ ፓርላማ ተካሂዷል። ውይይቱን የጠራውና ያዘጋጀው የአውሮፓ ፓርላማ የሰብአዊ መብቶች ኮሚቴ ሲሆን፣ይህም፤ በቅርቡ ወደ

https://p.dw.com/p/17R4T
Plenarsaal während einer Tagung im Europäischen Parlament in Brüssel am 28.03.2007. Foto: Guido Bergmann +++(c) dpa - Report+++
የአውሮጳ ምክር ቤት ብራስልስምስል picture-alliance/dpa

ኢትዮጵያ ለሚጓዘው የፓርላማው የልዑካን ቡድን ተጨማሪ ግንዛቤ ለመስጠት እንደሆነ ታውቋል። በውይይቱ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት አያያዝን የሚከታታሉ ኢትዮጵያውያንና ከዚህ ቀደም፤ በኢትዮጵያ በተደረጉ ምርጫዎች፣ የአውሮፓን ህብረት የምርጫ ታዛቢ ቡድን የመሩት ወ/ሮ አና ጎሜሽና ቴይስ በርማን የተገኙ ሲሆን፤ በብራሰልስ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተወካይም፤ በስብሰባው ተገኝተው የመንግሥታቸውን አቋም መግለጸቸውን ገበያው ንጉሤ የላከልን ዘገባ ያስረዳል።

ገበያው ንጉሤ

ተክሌ የኋላ

ሸዋዬ ለገሰ