የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ
ሐሙስ፣ ኅዳር 9 2014ማስታወቂያ
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ወደ ሚቆጣጠራቸዉ ላሊበላ እና ኮምቦልቻ ከተሞች ርዳታ ለማቅረብ ለሚፈልጉ ድርጅቶች የበረራ ፍቃድ መስጠቱን የኢትዮጵያ መንግስት አስታወቀ። የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ ለጋዜጠኞች እንደነገሩት በጦርነቱ ለተጎዳዉ ሕዝብ ርዳታ ለመስጠት የበረራ ፈቃድ የጠየቁ ድርጅቶች ፍቃዱ ተሰጥቷቸዋል። የርዳታዉን መጠንና ለችግረኛዉ የሚደርስበትን ጊዜ ግን ቃል አቀባዩ አልገለጡም። አምባሳደር ዲና በጋዜጣዊ መግለጫዉ የኬንያዉ ፕሬዝደንት ኡሑሩ ኬንያታ በቅርቡ አዲስ አበባ ዉስጥ ከጠቅላይ ሚንስትር ዓብይ አሕመድ ጋር ሥላደረጉት ዉይይት ዝርዝር ማብራሪያ መስጠት አልፈቀዱም።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ