1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ኤኮኖሚ

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በባለሙያዎች ሲገመገም

ረቡዕ፣ የካቲት 27 2011

ኢትዮጵያ ላለፉት ዓመታት ትከተለው በነበረው የምጣኔ ሀብት መርህዋ የብዙ ቢሊዮን ዶላር የውጭ ዕዳ ተሸካሚ ሆናለች። ሀገሪቱ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ምን ማድረግ አለባት? ለሚለው የምጣኔ ሀብት ምሁራን መፍትሄ የሚሉትን ጠቁመዋል።   

https://p.dw.com/p/3EYt6
Äthiopien Schuhfabrik Fabrik Herstellung Schuhe
ምስል Getty Images/Z. Abubeker

የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በባለሙያዎች ሲገመገም

ፕሮፈሰር ጌታቸው በጋሻው በዩናይትድ ስቴትስ ቺካጎ ክፍለ ግዛት ሀርፐር ኮሌጅ የምጣኔ ሀብት መምህር ናቸው። በዚያው በአሜሪካ ቨርጂኒያ በሚገኘው ኮሌጅ ኦፍ ዊሊያም ሜሪ መምህር የሆኑት ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝም በተመሳሳይ የትምህርት ዘርፍ ያስተምራሉ። በአንድ ሀገር እንዴት ኢንቨስትመንት ሊመጣ ይችላል? የምጣኔ ሀብት ለማምጣት ዋናው ትኩረት ምን ይሆን? ኢትዮጵያስ በአሁኑ ወቅት ምን ማድረግ አለባት? ለሚሉት ጥያቄዎች ባለሙያዎቹ ማብራሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ፕሮፌሰር ጌታቸው “የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በማንኛውም የኢኮኖሚ ስርዓት ለመገለጽ የማይችል፣ በየትኛውም የኢኮኖሚ ሞዴል ለመተንተን የማይቻል፣ አስቸጋሪ የሆነ እና በዘፈቀደ የሚካሄድ ነው ሲሉ ይተቻሉ”። ዶ/ር ብርሃኑ በበኩላቸው ያለፉት ዓመታት የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ “መንግስት መር” ነው ይላሉ። “በፓርቲ የተያዘ መንግስት የሚመራው የኢኮኖሚ እድገት ነው” ሲሉ ያክላሉ። 

የዋሽንግተኑ ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ያሰናውን ሙሉ ጥንቅር ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።   

መክብብ ሸዋ 

ተስፋለም ወልደየስ