1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ገለጻ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 3 2011

እሁድ ዕለት ማለዳ በኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ላይ በደረሰው አደጋ የድርጅቱ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ኃላፊ ዜጎቻቸው ለሞቱ ሃገራት አምባሳደሮችን ገለጻ አደረጉ። በተያያዘ ዜና ሌሎችም አየር መንገዶች ቦይንግ 737 አውሮፕላኖቻቸውን ከበረራ እያቆሙ መሆኑ እየተነገረ ነው።

https://p.dw.com/p/3EsBE
Äthiopien Flughafen Addis Ababa Ethiopian Airlines Boeing 737
ምስል Reuters/A.A. Dalsh

«ሌሎች ሃገራትም ቦይንግ 737ን ከበረራ እያገዱ ነው»

 የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከገዛው አራት ወራት ያልበለጠ ዕድሜ ያስቆጠረው ቦይንግ 737 ከአዲስ አበባ ናይሮቢ ለመብረር እንደተነሳ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ድንገት መከስከሱ እና የበረራ ሠራተኞቹን ጨምሮ ከ35 ሃገራት የመጡ ተሳፋሪዎቹ በመሉ አልተረፉም። የድርጅቱ ዓለም አቀፍ አገልግሎቶች ኃላፊ አቶ ኢሳያስ ወልደ ማርያም ለዲ ደብሊዩ ድርጅቱ አደጋው ከደረሰበት ጊዜ አንስቶ መረጃዎችን ሳያሰልስ ሲያቀርብ እንደነበረ አመልክተው፤ የየሃገራቱ አምባሳደሮችም በተመሳሳይ የአደጋው ሰለባ ዜጎቻቸውን በሚመለከት በበኩላቸው መተባበራቸውን ገልጸዋል። የአደጋውን መንስኤ የሚያጣሩ የአሜሪካ እና የኢትዮጵያ ባለሙያዎች እንደሚሆኑም አመልክተዋል።

በዛሬው ዕለትም ኖርዌጂያን ኤር ለጊዜው ቦይንግ 737 MAX 8 የመንገደኛ አውሮፕላኖቹን ከበረራ ማገዱን አስታውቋል። ውሳውን ያሳለፈውም ጉዳዩ በሚመለከታቸው በአውሮጳ የደህንነት ጉዳይ መዛኝ ተቋም ምክር መሆኑንም አመልክቷል። ከአዲስ አበባ ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዝርዝሩን ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ