1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ቅርስ የማስመለስ ጥረት እና ዩኔስኮ

ሰኞ፣ ሚያዝያ 29 2010

ኢትዮጵያ እኤአ በ1970 ዓ.ም ዩኔስኮ ያጸደቀውን የባህላዊ ቅርሶች እና ንብረቶች የባለቤትነት መብት ድንጋጌ በመጥቀስ ከዛሬ 150 ዓመታት በፊት ከመቅደላ የተዘረፉባትን ታሪካዊ እና ባህላዊ ቅርሶች ከእንግሊዝ ሙዝየሞች ለማስመለስ የጀመረችው ጥረት እንዳስደሰተው የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስ እና የባህል ማዕከል ዩኔስኮ አስታወቀ ::

https://p.dw.com/p/2xJev
Frankreich Paris Hauptquartier UNESCO
ምስል picture-alliance/AP/C. Ena

የኢትዮጵያ ጥያቄ በዓለም አቀፍ ሕግ መሠረት አግባብ ነው፤

                                                                                               

በድርጅቱ የዓለማቀፍ ቅርሶች ጥናት እና ጥበቃ ማዕከል የተንቀሳቃሽ  ቅርሶች እና ቤተመዘክሮች ዋና ሃላፊ በጉዳዩ ላይ ከመንግሥት ጋር ለመወያየት ዩኔስኮ ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለውም በተለይ ከዶቼ ቬለ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ ገልጸዋል :: በብሪታንያ ሙዝየሞች እና በግለሰቦች እጅ የሚገኙ ከጎንደር መቅደላ የተዘረፉት ውድ ባህላዊ ቅርሶች ከ 1.5 ቢልዮን ዶላር በላይ ዋጋ እንደሚተመኑ የሚጠቁሙ ጥናቶች አሉ ::  ዘጋቢያችን እንዳልካቸው ፈቃደ ከፍራንክፈርት ዝርዝሩን ልኮልናል።

እንዳልካቸው ፈቃደ

ሸዋዬ ለገሠ

ኂሩት መለሰ