1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብትና የካናዳው ጉባኤ

ረቡዕ፣ ግንቦት 28 2005

በካናዳ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ኮሚቴና ሌሎች የፖለቲካና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት የተካተቱበት የኢትዮጵያውያን የጋራ የትግል ሸንጎ ከዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋር በቅንጅት ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰ መሄዱ ተገልጿል።

https://p.dw.com/p/18k3s

በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት አያያዝ እንዲሻሻል በብሄራዊ መግባባት ላይ ያተኮረ የፖለቲካ ሂደት እንዲጀመር ተጠየቀ ። ኦታዋ ካናዳ ውስጥ ትናንት በኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብትና የዴሞክራሲያ ይዞታ ላይ የተነጋገረው ጉባኤ የፖለቲካው ሂደቱ ሰብዓዊ መብትና ዴሞክራሲያዊ ስርዓትን ማዕከል እንዲያደርግ አሳስቧል ። በካናዳ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ኮሚቴና ሌሎች የፖለቲካና የሲቪክ ማህበረሰብ አባላት የተካተቱበት የኢትዮጵያውያን የጋራ የትግል ሸንጎ ከዓለም ዓቀፉ የሰብዓዊ መብት ተሟጋች አምነስቲ ኢንተርናሽናል ጋር በቅንጅት ባዘጋጀው ጉባኤ ላይ የኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብት ይዞታ ከመሻሻል ይልቅ እየባሰ መሄዱ ተገልጿል ። ዝርዝሩን የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን አበበ ፈለቀ ልኮልናል ።

አበበ ፈለቀ

ሂሩት መለሰ

ተክሌ የኋላ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ