1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤት-99.6 ከመቶ

ማክሰኞ፣ ሰኔ 15 2002

የኢትዮጵያ ምርጫ ዉጤት የዶቸ ቬለ የአማርኛዉ ክፍል ሐላፊ ሉድገር ሻዶምስኪ እንደታዘበዉ ጉድ የሚያሰኝ ነዉ። 99.6 ከመቶ ድጋፍ።

https://p.dw.com/p/O072
ምስል AP

ኢትዮጵያ ዉስጥ ነብዩ መሐመድ፥ እየሱስ ክርስቶስ፥ ቅድስት ማርያም፥ቅድስ ገብርኤልም ባንድ ቢቆሙ እንኳን ይላል-ሻዶምስኪ-ይሕን ያሕል ደጋፊ የላቸዉም። ምክንያቱም ቢያንስ ሐይማኖት የለሽ ኢትዮጵያዉያን እነሱን አይደግፉምና።የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ ግን በ99.6 ከመቶ ድምፅ ተመረጠ ተብሏል።ኢሕአዴግ በዚሕ ዉጤት ተመረጠ መባሉ ለኢትዮጵያ ወዳጆችና ለኢትዮጵያ እርዳታ አቅራቢዎች ትልቅ ፈተና ነዉ።የሉድገር ሻዶምስኪን ሐተታ የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ሐይለ ሚካኤል ተርጉሞታል።

ሉድገር ሻዶምስኪ
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
አርያም ተክሌ