1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግስት ማስተባበያ እና የአ.ብ.ነ.ግ መግለጫ

ማክሰኞ፣ መጋቢት 1 2001

የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር ኦብነግ ፣ በሶማሌ ክልል ደገሀቡር አቅራቢያ ባለፈው ሳምንት በኢትዮጵያ ወታደሮች ላይ አደረስኩ ያለው ጥቃት ፍፁም ሀሰት ነው ሲል የኢትዮጵያ መንግስት አስተባበለ ።

https://p.dw.com/p/H8vd
ምስል AP GraphicsBank/DW

ባለፈው ሳምንት መጨረሻ ላይ የኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጭ ግንባር አ.ብ.ነ.ግ. በሰሜን ኦጋዴን ደገሀቡር አቅራቢያ በተዋጊዎቹ ና በኢትዮጵያ መንግስት ኃይሎች መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ሲል አስታውቋል ። በዚሁ መግለጫ ከረቡዕ የካቲት ሀያ አምስት ወዲህ በተካሄደው ውጊያ ሀያ አራት የኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውና ፣ ስድስት የአካባቢው አርብቶ አደሮች በኢትዮጵያ ወታደሮች መገደላቸውም ተጠቅሷል ። ኦብነግ ሰሞኑን ደገሀቡር አቅራቢያ ተካሄደ ስላለው ውጊያ እና በኢትዮጵያ መንግስት ወታደሮች ላይ ደረሰ ስላለው ጥቃት ዶይቼቬለ የጠየቃቸው የኢትዮጵያ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሚኒስትር ዴታ አቶ ኤርሚያስ ለገሰ የተባለው ሁሉ ሀሰት ነው ብለዋል ።