1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ መንግሥት፤ BBC እና ባንድ ኤይድ፤

ዓርብ፣ ጥቅምት 26 2003

የብሪታንያ ዜና ማሠራጫ ድርጅት (ቢቢሲ) አምና በመጋቢት ባቀረበው አንድ ዘገባ ላይ በ 1997 ዓ ም በነበረው ድርቅ ሳቢያ፣ በረሃብ ለተጎዳው ህዝብ ከባንድ ኤይድና ምዕራባውያን መንግሥታት የተሰጠውን እርዳታ፤

https://p.dw.com/p/Q05C
በ 1977 በደረሰው ድርቅና ብርቱ ረሃብ ሳቢያ በተተከሉ ድንኳኖች ተጠልለው የምግብ እርዳታና ክትባት ያገኙ የነበሩ እትዮጵያውያን ፣

ያኔ አማጺ ኃይል የነበረው ህ ወ ኀ ት በከፊል ለጦር መሣሪያ ግዢ አውሎታል ሲል መዘገቡ ይታወሳል።

ከሰሞኑ፣ BBC፣ ወቀሣው፣ በተለይ ከባንድ ኤይድ ጋር የተያያዘ እንዳልሆነና

« ከሠራነው በላይ ግልፅ ማድረግ ይገባን እንደነበረ እናምናለን» ሲል ይቅርታ መጠየቁ ተመልክቷል። ይቅርታው፣ ያተኮረው፣ ለግብረ-ሠናዩ ድርጅትና ለመሰሎቹ፣ ዋና ዓላማ ፣ በህዝብ ዘንድ የተዛባ አመለካከት እንዳያስከትል በማሰብ ነው።የሆነው ሆኖ፤ የ BBC ን ይቅርታ በተመለከተ፣ ታደሰ እንግዳው የኢትዮጵያን መንግሥት አቋም በመጠየቅ የሚከተለውን ዘገባ ልኮልናል።

ታደሰ እንግዳው

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ