1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለኢትዮጵያ አንድነት የድጋፍ መግለጫ ሰልፍ በብራስልስ

ሰኞ፣ ኅዳር 19 2009

በመቶ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ቤልጅየም መዲና፣ ብራስልስ በሚገኘው የአውሮጳ ህብረት ኮሚሽን እና በአውሮጳ ምክር ቤት ፊት ለፊት ዛሬ ሰልፍ አካሄዱ። እነዚሁ ከተለያዩ የአውሮጳ ሀገራት ወደ ብራስልስ የተጓዙት ኢትዮጵያውያን ለኢትዮጵያ ሰላም እና አንድነት፣ እንዲሁም፣  የሀገሪቱ  መንግሥት ለጀመረው የልማት ሂደት ያላቸውን ድጋፍ ገልጸዋል።

https://p.dw.com/p/2TOTB
Brüssel Europäische Kommission Außenansicht
ምስል picture-alliance/dpa/D. Kalker

Pro Äth. Regierung_Kundgebung in Brüssel - MP3-Stereo


ሰልፈኞቹ በተለያዩ ወቅቶች በብራስልስ የኢትዮጵያን መንግሥት በመቃወም ሰልፍ የሚያካሂዱ ቡድኖች የሚያስተጋቡት መረጃ የተሳሳተ መሆኑን ለአውሮጳ ህብረት ግልጽ የማድረግ ዓላማ እንዳላቸውም ለዶይቸ ቬለ አስታውቀዋል። የብራስልስ ወኪላችን የሰልፉን አስተባባሪዎች አነጋግሮዋል።
ገበያው ንጉሤ

አርያም ተክሌ

ኂሩት መለሰ