1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያ ሃይቆችና የተደቀነባቸው የመድረቅ አደጋ፣

ረቡዕ፣ ግንቦት 11 2002

በግምት 10 ሚሊዮን የሚሆን የቡሩንዲ፣ የታንዛንያ፣ የዛምቢያና የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፓብሊክ ህዝብ፤ የሚጠጣ ውሃና ለምግብ የሚሆን አሣ ያገኝበታል።

https://p.dw.com/p/NS7B
ምስል AP

በያመቱ 200,000 ቶን ያህል አሣ ፣ በአመዛኙም ሰርዲን ይታፈስበታል። በታላቁ የምሥራቅ አፍሪቃ ስምጥ ሸለቆ ከሚገኙት ታላላቅ ሃይቆች መካከል አንዱ፣ በዓለም ውስጥም ጨዋማነት ከሌላቸው ቀላዮች መካከል በስፋት 2ኛ ወይም ሦስተኛ፤ በጥልቀት ደግሞ ከሳይቤሪያው ባይካል ቀጥሎ ሁለተኛ የሆነው፣ የታንጋኒካ ሃይቅ!

ከሰሜን እስከ ደቡብ 673 ኪሎሜትር ርዝማኔ፤ በአማካይ 50 ኪሎሜትር ስፋት፣ በአጠቃላይ 1,828 የጠረፍ ርዝማኔ፣ 18,900 ኪዩቢክ ኪሎሜትር የውሃ መጠን፣ እንዲሁም፣ በአማካዩ 570 ፣ በሰሜናዊው ከፊልም 1,470 ሜትር ያህል ጥልቀት አለው። ይህ ሀይቅ፤ አሁን፤ አሁን ፣ ግለቱ እየጨመረ በመምጣቱ፣ የላይኛው የሃይቁ ውሃ፣ 26 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በመድረሱ፣ የወደፊቱ ሁኔታ ያሠጋል ሲሉ፣ ጥናት ያካሄዱ ጠበብት ከሰሞኑ ያወጡት መግለጫ፣ ከሳይንስ ነክ ዐበይት መወያያ አርእስት መካከል አንዱ ለመሆን ችሏል።

ምድራችን ፣ ውቅያኖሶችም ፤ ሀይቆችም፣ ግለታቸው እየጨመረ በመሄዱ፣ የሳይንስና የተፈጥሮ አካባቢ ጠበብትን በአኅጉርና ዓለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ሲያነጋግር መቆየቱ የሚዘነጋ አይደለም። አሁን የሃይቆችን ይዞታ ካነሣን፣ ኢትዮጵያንም ሊያሳስባት እንደሚገባ የሚያጠራጥር አይደለም። የምድር ግለት መጨመር፤ የበረሃ መሥፋፋት ብቻ ሳይሆን የሃይቆች ይዞታም መላ እንዲፈለግለት የግድ የሚል ነው። ሃይቆች እስከመድረቅ መድረሳቸው ይታወቃልና! ኢትዮጵያ ውስጥ ሃይቆች በምን ምክንያቶች ነው ለድርቅ የሚጋለጡት? አብነቱስ ምንድን ነው? አድማጮቻችን ፣ በዛሬው ሳይንስና ኅብረተሰብ ቅንብራችን፣ በዚህ ርእስ ዙሪያ፣ አሁን በጀርመን ሀገር ትምህርታቸውን በከፍተኛ ደረጃ በመከታተል ላይ የሚገኙ አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሙያ አነጋግረናል።

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ