1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢትዮጵያና የጀርመን መሪዎች መግለጫ

ረቡዕ፣ ኅዳር 24 2007

በጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የሚመሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ልዑካን ፤ ከጀርመን መራኂተ መንግሥት ወ/ሮ አንጌላ ሜርክልና ሌሎችም ባለሥልጣናት ጋር በጋራና በአፍሪቃ ቀንድ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸው ተገልጿል። የሁለቱ ሃገራት ባለሥልጣናት ሕንጻ ውስጥ

https://p.dw.com/p/1Dyuy
ምስል Reuters/H. Hanschke

ተገናኝተው ሲነጋገሩ ከውጭ ፣ በጀርመን ሀገር የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የተቃውሞ ሰልፍ ማሳየታቸው ታውቋል። ለሥርጭት ወደ ስቱዲዮ ከመግባታችን በፊት ስልክ የደወልኩለት የበርሊኑ ዘጋቢአችን ይልማ ኃይለ ሚካኤል ፣ ጠ/ሚንስትር አቶ ኃይለማርያም ለጀርመን ባለወረቶች መግለጫ መስጠታቸውን ነበረ የገለጸልኝ።በተያያዘ ዜና የጀርመንዋ መራሒተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል የጀርመን ኩባንዮች አፍሪቃ ዉስጥ የላቀ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ጠየቁ።ሜርክል ዛሬ የኢትዮጵያዉን ጠቅላይ ሚንስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝን ካነጋገሩ በኋላ በጋራ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት አዉሮጳ፤ አፍሪቃ ዉስጥ ባሁኑ ወቅት ያለዉ አጋጣሚ ሊያመልጣት አይገባም።የኢትዮጵያዉ ጠቅላይ ሚንስትርም የጀርመን ኩባንዮች ሐብታቸዉን ኢትዮጵያ ዉስጥ ሥራ ላይ እንዲያዉሉ ጠይቀዋል።በጠቅላይ ሚንስትር ኃይለ ማርያም የሚመራዉ የኢትዮጵያ መንግሥት የመልዕክተኞች ቡድን ጀርመንን እየጎበኘ ነዉ።

ይልማ ኃ/ሚካኤል

ተክሌ የኋላ

ነጋሽ መሐመድ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ