1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኢራንና የሳዑዲ አረቢያ ዉዝግብ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 25 2008

የሳዑዲ አረቢያ መንግሥት ባሸባሪነትና የተቃዉሞ ሠልፍ በማደራጀት የወነጀላቸዉን አርባ-ሰባት ዜጎቹን በሞት መቅጣቱ ከተለያዩ ሃገራት ተቃዉሞ፤ ከኢራን ዉግዘትና የዲፕሎማሲ ዉዝግብ ገጥሞታል።

https://p.dw.com/p/1HXou
Iran Protest in Teheran gegen Hinrichtung in Saudi-Arabien
ምስል Getty Images/AFP/A. Kenare

[No title]

በሞት ከተቀጡት እንዱ የሺዓ ሃይማኖታዊ መሪ ሼሕ ነሚር አል ነሚር መሆናቸዉ ያስቆጣዉ የኢራን ሕዝብ ትንናት በቴሕራን የሳዑዲ አረቢያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢን እሳት ለኩሶበታል። ሪያድ በኤምባሲዋ ላይ የተቃጣዉን ጥቃት ለመበቀል ዲፕሎማቶችዋን ከቴሕራን ሥታስወጣ፤ በሳዑዲ አረቢያ የኢራን ዲፕሎማቶችም በ48 ሰዓታት ዉስጥ ከግዛትዋ እንዲወጡ አዛለች።የኢራን መሪዎች የሳዑዲ አረቢያን እርምጃ አጥብቀዉ አዉግዘዋል።የሁለቱን ሐገራት ዉዝግብ በተመለከተ ነጋሽ መሐመድ የጂዳ ተባባሪ ዘጋቢያችን ነቢዩ ሲራክን በሥልክ አነጋግሮታል።

ነቢዩ ሲራክ

ነጋሽ መሐመድ

ማንተጋፍቶት ስለሺ