1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

ለጠቅላይ ሚንስትርነት የታጨዉ አልታወቀም

ማክሰኞ፣ መጋቢት 11 2010

የግንባሩ ፅሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ሥራ የአስፈፃሚዉ ስብሰባ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊን መስመር በሚያጠናክር መልኩ ተጠናቀቀ ከማለት ሌላ፤ ተሰብሳቢዎች ሊቀመንበር እና ጠቅላይ ሚንስትር ሥለማጨት አለማጨታቸዉ ያለዉ ነገር የለም።

https://p.dw.com/p/2udnc
Karte Äthiopien englisch

(Beri.AA) EPRDF Council meeting - MP3-Stereo

      

የኢትዮጵያ ገዢ ፓርቲ የኢሕአዴግ ምክር ቤት ሥብሰባ ዛሬ ተጀምሯል።ተሰብሳቢዎች የግንባሩን ሊቀመንበር እና የሐገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር ይመርጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።የግንባሩ ሥራ-አስፈጻሚ ኮሚቴ ካለፈዉ መጋቢት ሁለት ቀን ጀምሮ ያደረገዉን ሥብሰባ ትናንት አጠናቅቋል።ሥራ አስፈፃሚዉ የግንባሩን ሊቀመንበር እና የሐገሪቱን ጠቅላይ ሚንስትር ለሚመርጠዉ  ምክር ቤት እጩ ያቀርባል ተብሎ ሲጠበቅ ነበር።ይሁንና የግንባሩ ፅሕፈት ቤት ዛሬ ባወጣዉ መግለጫ ሥራ የአስፈፃሚዉ ስብሰባ የአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊን መስመር በሚያጠናክር መልኩ ተጠናቀቀ ከማለት ሌላ፤ ተሰብሳቢዎች ሊቀመንበር እና ጠቅላይ ሚንስትር ሥለማጨት አለማጨታቸዉ ያለዉ ነገር የለም።አንድ የሕዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ የቀድሞ ታጋይ እንደሚሉት ግን የኢሕአዴግ ሹማምንት የሥልጣን ሽኩቻ ገጥመዋል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሐመድ

ኂሩት መለሰ