1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍቃሪ ናዚዎች ጥቃት በመግልን

ዓርብ፣ ነሐሴ 18 1999

ጥቃቱ ጀርመናውያን ለውጭ ዜጎች ያላቸውን አመለካከት ዳግም ጥያቄ ምልክት ውስጥ አስገብቷል ።

https://p.dw.com/p/E0c0
ጥቃት የደረሰበት ህንዳዊ..
ጥቃት የደረሰበት ህንዳዊ..ምስል picture-alliance/dpa
በቁጥር ሀምሳ የሚሆኑ ቀኝ አክራሪ ጀርመናውያን ስምንት ህንዳውያንን በከተማይቱ የበዓል ዝግጅት ይካሄድበት ከነበረበት ስፍራ ተተናኩለው ከዚያም በከተማይቱ አደባባይ እያሳደዱ ጉዳት አድርሰውባቸዋል ። በወቅቱም « የውጭ ዜጎች ከሀገራችን ይውጡ » « እዚህ የሚገዛው የጀርመን ብሄርተኝነት ነው ። » እያሉ ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ይጮሁ ነበር ።