1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል

ሰኞ፣ ጥር 21 2010

በአዲስ አበባ ትላንት የተጀመረው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ማምሻውን ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡ በጉባኤው ከተነሱት ነጥቦች መካከል በሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ህብረቱን ለማሻሻል የቀረበው እቅድ አንዱ ነው፡፡

https://p.dw.com/p/2rjDW
Äthiopien Hauptqartzier der Afrikanischen Union in Addis Ababa
ምስል Reuters/T. Negeri

የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ጉባኤ ዛሬ ይጠናቀቃል

ከጉባኤው በተጓዳኝ ስለ ደቡብ ሱዳን ጉዳይ የተደረገው ስብሰባ የሚጠቀስ ነው፡፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) እና የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን የደቡብ ሱዳን የሰላም ስምምነትን በሚጥሱ ኃይሎች ላይ ጠንካራ እርምጃ ሊወሰድ እንደሚገባ አቋሞቻቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡ የአፍሪቃ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ ማሀማት የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ወገኖች የሰላም ስምምነት እንዲደርሱ፣ አለበለዚያ የአፍሪቃ ህብረት ማዕቀብ ሊጣልባቸው እንደሚችል በመክፈቻው ንግግራቸው  አሳስበዋል። ለደቡብ ሱዳን ውዝግብ ህብረቱ ወይም የምሥራቅ አፍሪቃ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) የሚያደርጉትን ጥረትም የተመድ እንደሚደግፍ ዋና ጸሐፊ አንቶንዮ ጉተረሽ አስታውቀዋል።  የአዲስ አበባው ወኪላችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ጉባኤውን ተከታትሎታል፡፡ ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።  

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ተስፋለም ወልደየስ

ሂሩት መለሰ