1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል
ሳይንስ

የአፍሪቃ የፈጠራ ሳምንት ዝግጅት

ረቡዕ፣ ነሐሴ 29 2011

ከሰሞኑ የአፍሪቃ የፈጠራ ሳምንት በቅርቡ እንደሚካሄድ ያመላከተ መርሃግብር አዲስ አበባ ላይ ተካሂዷል። የአፍሪቃ የፈጠራ ሳምንት በመላው አፍሪቃ ያለውን የፈጠራ እንቅስቃሴ በማጠናከር አህጉረ አፍሪቃን የበለፀገች ለማድረግ ወደፊት ለማራመድ የታቀደ መሆኑን የመርሃግብሩ አዘጋጆች ይናገራሉ።

https://p.dw.com/p/3P0gm
African Union Hauptquartier in Addis Abeba
ምስል AFP/Getty Images/J. Vaughan

ሳይንስና ቴክኒዎሎጂ

 መርሃግብሩ በአፍሪቃ የሚታዩ የፈጠራ ጅምሮችን በማበልፀግ በመላው አህጉር እንዲስፋፉ የማድረግ ዓላማ እንዳለውም ያመለክታሉ። አይ ቢ ኤ ኢትዮጵያ ከኢኖቬሽን እና ቴክኒዎሎጂ ሚኒስቴር፤ ከአፍሪቃ ሕብረት፣ ከኖርዌይ ኤምባሲ እና ከሌሎች ጋር በመተባበር የሚያዘጋጁት ይህ መርሃግብር በመጪው 2012 ዓም ከጥቅምት 17 እስከ ጥቅምት 22 ድረስ በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ በአፍሪቃ ሕብረት ዋና ጽሕፈት ቤት ይካሄዳል። ይህ መርሃግብር ይፋ በሆነበት መድረክ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ወጣት የፈጠራ ባለሙያዎችን አነጋግሮ ለዕለቱ የሳይንስ እና ቴክኒዎሎጂ መሰናዶ አጠናቅሯል። 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ሸዋዬ ለገሠ