1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣት መሪዎች ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 26 2008

51 ወጣት ኢትዮጵያውን በተካፈሉበት በዚህ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንደሚገኙ ተነግሮ የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በመዝጊያው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።

https://p.dw.com/p/1JaQg
USA Oberster Gerichtshof mit Flagge auf Halbmast in Washington
ምስል picture-alliance/dpa/EPA/M. Reynolds

[No title]


አፍሪቃውያን ወጣት «መሪዎች» የተባሉት የአህጉሪቱ ወጣቶች የተሳተፉበት ጉባኤ ትናንት በዋሽንግተን ዲሲ ተጀመረ ። በዚሁ ጉባኤ ላይ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ49 የአፍሪቃ ሃገራት የተውጣጡ ወደ 1 ሺህ የሚጠጉ ወጣቶች እና የአሜሪካን ከፍተኛ ባለሥልጣናት ተገኝተዋል ። 51 ወጣት ኢትዮጵያውን በተካፈሉበት በዚህ ጉባኤ መክፈቻ ላይ እንደሚገኙ ተነግሮ የቀሩት የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በመዝጊያው ላይ ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል ።ጉባኤው ላይ የተገኙት ወጣቶች ላለፉት 6 ሳምንታት የተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ዩኒቨርስቲዎችን ጎብኝተዋል። የዋሽንግተን ዲሲው ዘጋቢያችን መክብብ ሸዋ ዝርዝር ዘገባ አለው ።
መክብብ ሸዋ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ