1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ወጣት መሪዎች በዋይት ሃዉስ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 30 2007

በዋሽንግተን ዲሲ የፕሬዚዳንት ኦባማ የአፍሪቃ ወጣቶች ዓመታዊ ጉባኤ ባለፈዉ ማክሰኞ ተከፈተ። ወጣቶቹ ከአፍሪቃ አህጉር ተመርጠዉ ትምህርታቸዉን መከታተል ከጀመሩ ስድስት ሳምንታትን አስቆጥረዋል።

https://p.dw.com/p/1GBCd
Beau Biden Trauerfeier
ምስል Getty Images

[No title]


ከ 30 ሺህ ተወዳዳሪዎች መካከል ተመርጠዉ የመጡት እነዙህ ወጣቶች 500 መሆናቸዉ ነዉ የተነገረዉ። የአፍሪቃዉያን ወጣት መሪዎች ዉጥን ማጎልበቻ መረብ በመባል የሚታወቀዉ ዓመታዊ መረሃ -ግብር በፕሬዚዳንት ኦባማ አማካኝነት ከተጀመረ ሁለት ዓመታትን አስቆጥሮአል። መሰል ማዕከል በአፍሪቃ ጋና ከተማ የተከፈተ ሲሆን ሌሎች ተጨማሪ ማዕከሎች በዓመቱ መጨረሻ እንደሚከፈቱ ፕሬዚዳንቱ ገልፀዋል። በቀድሞዉ የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚዳንት በኔልሰን ማንዴላ ስም የተሰየመዉና የማንዴላ አርዓያነት የተባለዉ ይህ ተቋም ሶስት ስልጠናዎችን በማኅበራዊ መገናኛ መረብ ማዘጋጀቱም ታዉቋል። በተቋሙ የሰልጣኞቹ ቁጥር በእጥፍ ጨምሮ በመጭዉ ዓመት 1000 እንደሚሆኑ ፕሬዚዳንት ኦባማ ቃል መግባታቸዉ ታዉቋል ።


መክብብ ሸዋ
አዜብ ታደሰ
ነጋሽ መሃመድ