1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ችግር፥ የተገባዉ ቃልና የቡድን ሥምንት ጉባኤ

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 1 2000

የአፍሪቃ ችግር፥ የተገባዉ ቃልና የቡድን ሥምንት ጉባኤ

https://p.dw.com/p/EYQt
የሆካይዶ ጉባኤተኞችምስል AP

የቀድሞዉ የፈረንሳይ ፕሬዝዳት ቫለሪ ጄስካ ደ ኢስታ በ1975 (ዘመኑ በመሉ እንደ አዉሮጳዉያኑ አቆጣጠር ነዉ) ራምቡዮ-ፈረንሳይ ላይ የአምስት የሐገራቸዉን ወዳጆች ሐገራት መሪዎች የጋበዙት የነዳጅ ዋጋ ንረት ሥላደረሰዉ የምጣኔ ሐብት ድቀት መላ ለማፈላለግ ነበር።ልክ እንደያኔዉ ነዳጅ ዘይት በተወደደበት፤ የምግብ ዋጋ በናረበት፥ የአፍሪቃ ድሕነት በጠናበት፥የተፈጥሮ ሐብት በተመናመነ-በተበከለበት ዘንድሮ ሥለ-አለም ሊበይኑ ሰኞ ሆካይዶ-ጃፓን ላይ ተሰበሰቡ።-የቡድን ስምት አባል ሐገራት መሪዎች።ጤና ይስጥልኝ እንደምን ዋላችሁ።የሆካይዶዉ ጉባኤ መነሻ-የአለም ሁኔታ ማጣቀሻ፥ የአፍሪቃ ችግር መድረሻችን ነዉ አብራችሁኝ ቆዩ።