1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ተፈናቃዮች

ረቡዕ፣ ጥር 29 2011

ከስድስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎቿ በተፈናቀሉባት አፍሪቃ ተፈናቃዮችን ለመንከባከብ የሚደረገው ሥራ እዚህ ግብ የሚባል አለመኾኑ ተገለጠ። ኦክስፋም ፓን አፍሪቃ አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው ስምንተኛው የዜጎች ጉባኤ ላይ እየመከሩ ያሉት አፍሪቃውያን በውይይታቸው አፍሪቃ በተለይ ስደተኞች እና የስደተኞች አያያዝ ላይ እንድታተኩረም አበክረው ጠይቀዋል።

https://p.dw.com/p/3CriA
Äthiopien Addis Abeba  OXFAM
ምስል DW/S. Muchie

MMT Beri. [A.A- Oxfam the 8th Citizens Conference ] - MP3-Stereo

ከስድስት ሚሊዮን በላይ ነዋሪዎቿ በተፈናቀሉባት አፍሪቃ ተፈናቃዮችን ለመንከባከብ የሚደረገው ሥራ እዚህ ግብ የሚባል አለመኾኑ ተገለጠ። ኦክስፋም ፓን አፍሪቃ አዲስ አበባ ውስጥ ባዘጋጀው ስምንተኛው የዜጎች ጉባኤ ላይ እየመከሩ ያሉት አፍሪቃውያን በውይይታቸው አፍሪቃ በተለይ ስደተኞች እና የስደተኞች አያያዝ ላይ እንድታተኩረም አበክረው ጠይቀዋል። ጉባኤው፦ 32 ኛው የአፍሪቃ ኅብረት የመሪዎች ጉባኤ ከመከናወኑ በፊት የተኪያሄደው የኅብረቱ ዋና ዋና ሥራዎች እንዴት እየተከናወኑ ነው በሚል በዜጎች መርምሮ ለመፈተሽ መኾኑ ተገልጧል። 
ሰለሞን ሙጬ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ኂሩት መለሰ