1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ቀንድ አገራት የሰብዓዊ መብት ይዞታ

ማክሰኞ፣ ኅዳር 1 2002

በኤርትራና በአፍሪቃ ቀንድ ሰብዓዊ መብትን ለማስከበርና ዲሞክራሲን ለመገንባት የአሜሪካና የአውሮፓ የጋራ ፖሊሲ አስፈላጊነት ላይ በማተኮር ትናንት ብራሰልስ ውስጥ የተጀመረው ስብሰባ ዛሬ ማምሻውን ይጠናቀቃል ።

https://p.dw.com/p/KTMV
ምስል picture-alliance/ dpa

ስብሰባው በኤርትራ በሚደርሰው የሰብዓዊ መብት ጥሰት ና በችግሩ ማቃለያ የመፍትሄ ሀሳቦች ላይ እንደሚያተኩር ቢገለፅም የኢትዮጵያ ጉዳይም መወሳቱ አልቀረም ። ስብሰባው በማጠቃለያው የአካባቢውን ችግር ለማቃለል ይረዳል የተባለ የፖሊሲ ሀሳብ ለአውሮፓና አሜሪካ ፖሊሲ እውጭች ያቀርባል ተብሎ ይጠበቃል ።

ገበያው ንጉሴ ፣ ሂሩት መለሰ