1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ ረሐብና ሕብረቱ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 10 2003

የአፍሪቃ ሕብረት የሠላምና የፀጥታ ኮሚሽን በበኩሉ ለሶማሊያ ረሐብተኞች ርዳታ የሚያከፋፍሉ ወገኖችን ደሕንነት የሚጠብቅ ከ3 ሺሕ በላይ ተጨማሪ ሠላም አስከባሪ ጦርና ፖሊስ ለማዝመት ወስኗል

https://p.dw.com/p/RgFz
ርዳታዉ ጠባቂ ይሻዋልምስል AP

ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ ተጨማሪ ርዳታ ካልደረሰ የበርካታ ሰዉ ሕይወት እንደሚጠፋ የአፍሪቃ ሕብረት ኮሚሽን ፕሬዝዳት ዣን ፒንግ አስጠነቀቁ።ፒንግ እንደሚሉት ሕብረታቸዉ ለረሐብ ለተጋለጠዉ ሕዝብ መርጃ 2.4 ቢሊዮን ዶላር እያሰባሰበ ነዉ።ምሥራቅ አፍሪቃ ዉስጥ አስራ ሁለት ሚሊዮን በላይ ሕዝብ ለረሐብ ተጋልጧል።የአፍሪቃ ሕብረት የሠላምና የፀጥታ ኮሚሽን በበኩሉ ለሶማሊያ ረሐብተኞች ርዳታ የሚያከፋፍሉ ወገኖችን ደሕንነት የሚጠብቅ ከ3 ሺሕ በላይ ተጨማሪ ሠላም አስከባሪ ጦርና ፖሊስ ለማዝመት ወስኗል።ታደሠ እንግዳዉ ዝር ዝር ዘገባ አለዉ።

ታደሰ እንግዳዉ

ነጋሽ መሐመድ

ተክሌ የኋላ