1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃ መገናኛ ብዙሃን

ሐሙስ፣ ጥቅምት 17 2009

አፍሪቃ የልማት እቅዶችዋን ከዳር ለማድረስ ፣ ትልቁን ድርሻ የሚይዙት መገናኛ ብዙሃን በገለልተኝነት የሚዘግቡባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እና ለዘርፉም ትኩረት መስጠት እንደሚገባት ስብሰባው ጠቁሟል።

https://p.dw.com/p/2RnnK
Pretoria Südafrika ARCHIVBILD
ምስል picture alliance/augenklick

 

በአፍሪቃ ክፍለ ዓለም ጋዜጤኞችን ከህዝቡ ጋር የሚያቀራርብ የመገናኛ ብዙሃን ባለመኖሩ ህዝቡ የልማቱም ሆነ የነጻነቱ ተጠቃሚ ሊሆን አለመቻሉ ተገለፀ። ይህ የተገለፀው ፕሪቶርያ ደቡብ አፍሪቃ ውስጥ በተካሄደው የጋዜጠኝነት ሥልጠና የሚሰጡ አፍሪቃውያን መምህራን እና ጋዜጠኞች በተሳተፉበት ስብሰባ ላይ ነው ። አፍሪቃ የልማት እቅዶችዋን ከዳር ለማድረስ ፣ ትልቁን ድርሻ የሚይዙት መገናኛ ብዙሃን በገለልተኝነት የሚዘግቡባቸውን ሁኔታዎች ማመቻቸት እና ለዘርፉም ትኩረት መስጠት እንደሚገባት ስብሰባው ጠቁሟል። የደቡብ አፍሪቃው ዘጋቢያችን ስብሰባውን ተከታትሎ ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል ።

መላኩ አየለ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ