የአፍሪቃ ሕብረት የሚንስትሮች ሥብሰባ
ረቡዕ፣ ጥር 18 2008ማስታወቂያ
የአፍሪቃ ሕብረት አባል ሐገራት የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች ዛሬ አዲስ አበባ ዉስጥ ተሰብሰበዋል።ሚንስትሮቹ ነገን ጨምሮ ለሁለት ቀን በሚያደርጉት ሥብሰባ የፊታችን ቅዳሜ ለሚጀመረዉ የመሪዎች ጉባኤ የመነጋገሪያ ርዕሶችን ያረቅቃሉ።የሚንስትሮቹ ሥብሰባ ዛሬ ሲጀመር የወቅቱ የሕብረቱ የሚንስትሮች ምክር ቤት ሊቀመንበር የዚምባቡዌዉ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ለባልደረቦቻቸዉ እንደነገሩት ሕብረቱን ለማጠናከር አባል ሐገራት መዋጮቸዉን መክፈል አለባቸዉ።የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ በቅርቡ የናጄሪያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ሆነዉ የተሾሙትን የቀድሞዉ የአፍሪቃ ሕብረት የሠላምና የፀጥታ ኮሚሽነር ራምታ ላማምራን አነጋግሮ ያጠናቀረዉን ዘገባ ልኮልናል።
ጌታቸዉ ተድላ ሐይለ ጊዮርጊስ
ነጋሽ መሐመድ
አርያም ተክሌ