1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአፍሪቃውያንን ብሔራዊ ስሜት የሚገመግም መፅሀፍ ተመረቀ

ሐሙስ፣ የካቲት 7 2011

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከጨበጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ያከናወነቻቸው ተግባራት አፍሪቃ በለውጥ ሒደት ላይ ለመሆኗ አንድ ምልክት እንደሆነም ናይጄሪያዊው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተመራማሪ ዶክተር ሚካኤል አሞሕ ተናገሩ። ተመራማሪው ይኸን ያሉት በአፍሪቃ ብሔራዊ ሥሜት፤ የሀገረ-መንግሥት እሳቤ ላይ ያተኮረ መጽሐፋቸውን ባስመረቁበት ወቅት ነው።

https://p.dw.com/p/3DNYi
Michael Amoah Sachbuchautor aus Nigeria
ምስል DW/Hana Demissie

ጸሐፊው የኢትዮጵያን ጥረት አድንቀዋል

ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ሥልጣን ከጨበጡ ወዲህ ኢትዮጵያ ያከናወነቻቸው ተግባራት አፍሪቃ በለውጥ ሒደት ላይ ለመሆኗ አንድ ምልክት እንደሆነም ናይጄሪያዊው የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተመራማሪ ዶክተር ሚካኤል አሞሕ ተናገሩ። ተመራማሪው ይኸን ያሉት በአፍሪቃ ብሔራዊ ሥሜት፤ የሀገረ-መንግሥት እሳቤ ላይ ያተኮረ መጽሐፋቸውን ባስመረቁበት ወቅት ነው።  

በጎሳ የተከፋፈለን አገር ለማዋሐድ ፈታኝ እንደሆነ የሚናገሩት ጸሀፊው ጠቅላይ ምኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለአካባቢው አዲስ ርዕይ ይዘው መጥተዋል የሚል ዕምነት አላቸው። አዲሱ መጽሐፋቸው ግብፅ፤ ሱዳን፤ ቡርኪና ፋሶ፤ ቡሩንዲ፤ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ማሊን ጨምሮ በሌሎች ስምንት የአፍሪቃ አገሮች የታየውን የፖለቲካ ቀውስ ዳሷል። ናይጄሪያዊው ሚካኤል አሞህ ከዚህ ቀደም በርከት ያሉ ጥናታዊ ፅሁፎች እና መጻህፍት ለህትመት አብቅተዋል። 
ሐና ደምሴ
ነጋሽ መሐመድ