1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር ጉዞ ሙከራ

እሑድ፣ ጥር 24 2007

የአዲስ አበባ ቀላል የባቡር ጉዞ እሁድ ጥር 24 ቀን፤ 2007 ዓም ከቃሊቲ አዲስ አበባ የሙከራ ጉዞ መጀመሩን ተዘገበ። የሙከራ ጉዞው ለሚቀጥሉት ወራት እንደሚቀጥልም ተገልጧል።

https://p.dw.com/p/1EUCF
Äthiopien Stadtbahn Probefahrt in Addis Abeba
ምስል DW/Yohannes G. Egiziabher

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር እሁድ ጥር 24 ቀን፤ 2007 ዓም ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ እና ሌሎች ባለሥልጣናት በተገኙበት የሙከራ ጉዞ ማድረጉን የአዲስ አበባው ወኪላችን በላከልን ዘገባ ጠቅሷል። የሙከራ ጉዞው ቢያንስ ለሚቀጥሉት ሦስት ወራት ማለትም የወርሃ ሚያዝያ ማብቂያ እና የግንቦት ወር መጀመሪያ ድረስ እንደሚቆይም ተገልጧል። የሙከራ ጉዞው ደኅንነቱ አስተማማኝ መሆኑ ከተረጋገጠ በኋላ ለህዝብ አገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል። ሙሉ ዘገባውን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር እንደሚከተለው ያቀርበዋል።

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ