1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

እርዳታ ለጎንደር ተፈናቃዮች

ሐሙስ፣ የካቲት 14 2011

ተፈናቃዮቹ ድጋፉ በቂ አይደልም እያሉ ቢሆንም ከክልሉ ባቀረበልን ጥያቄ መሠረት እያቀረብን ነው ሲሉ ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለ DW ተናግረዋል፡፡ የሚደረገው ድጋፍ ፍትሃዊነት ለመከታተልም በመላሃገሪቱ 6 ቡድኖች ተሰማርተው አሰሳ እደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡

https://p.dw.com/p/3Do15
12.06.2013 DW Online Karten Basis Äthiopien Englisch

ብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአማራ ክልል ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በማእከላዊ እና ምእራብ ጎንደር ዞኖች ለተፈናቀሉ  45 ሽህ 922 ዜጎች ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ የሰብአዊ ድጋፎችን  መስጠት መጀመሩን አስታውቋል፡፡ ድጋፉ በየወሩ ይቀጥላል ያለው ኮሚሽኑ በመልሶ ማቋቋም ሥራዎች ላይም እንደሚሳተፍ ተናግሯል፡፡ ተፈናቃዮቹ ድጋፉ በቂ አይደልም እያሉ ቢሆንም ከክልሉ ባቀረበልን ጥያቄ መሠረት እያቀረብን ነው ሲሉ ኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት እና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ደበበ ዘውዴ ለ DW ተናግረዋል፡፡ ኢትዮጵያ በድርቅ፡ በጎርፍ ፡ በመሬት መንሸራተት እና መሰንጠቅ ዜጎቿን ከከፋ ጉዳት ለመታደግ እየሠራች ቢሆንም አሁን አሁን ደግሞ ግጭት ያስከተለው መፈናቀል ለሰብአዊ ድጋፍ የሚደረገውን ሥራ የበለጠ እንዲሰፋ አድርጎታል፡፡ የሚደረገውን ድጋፍ ፍትሃዊነት ለመከታተልም በመላሃገሪቱ 6 ቡድኖች ተሰማርተው አሰሳ እደረጉ መሆኑን ኮሚሽኑ ገልጿል፡፡ የአዲስ አበባው ወኪላችን ሰሎሞን ሙጬ ዝርዝር ዘገባ አለው ።

ሰሎሞን ሙጬ

ኂሩት መለሰ

ሸዋዬ ለገሠ
 

ቀጣዩን ክፍል ዝለለዉ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ

ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ