1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአይቮሪ ኮስት ጠቅላይ ምኒስትር አማዱ ጎን ኩሉባሊ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

ሐሙስ፣ ሐምሌ 2 2012

የአይቮሪ ኮስት ጠቅላይ ምኒስትር አማዱ ጎን ኩሉባሊ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። ጠቅላይ ምኒስትሩ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ስብሰባ ላይ ሳሉ ሕመም ተሰምቷቸው ረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

https://p.dw.com/p/3f48g

የአይቮሪ ኮስት ጠቅላይ ምኒስትር አማዱ ጎን ኩሉባሊ በድንገት ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።ጠቅላይ ምኒስትሩ ከአገራቸው ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር ስብሰባ ላይ ሳሉ ሕመም ተሰምቷቸው ረቡዕ ሐምሌ 2 ቀን 2012 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ከሁለት ወራት ሕክምና በኋላ ከፈረንሳይ የተመለሱት በቅርቡ ነበር።  ጠቅላይ ምኒስትሩ ለመጪው ምርጫ ገዢውን ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ሊወዳደሩ ታጭተው ነበር። ፕሬዝዳንት አላሳን ዋታራን ይተካሉ ተብለው ይጠበቁ የነበሩት የ61 አመቱ ኩሉባሊ ምን ለሞት እንዳበቃቸው የታወቀ ነገር የለም።