1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት ታዛቢዎች ቡድን ሀላፊ መግለጫ

ሰኞ፣ ግንቦት 9 2002

የፊታችን ዕሁድ ግንቦት 15 , 2002 ዓመተ ምህረት የሚካሄደው 4 ተኛው አገር አቀፍ ምርጫ ለአጭር ጊዜ የሚታዘቡ የአውሮፓ ህብረት የምርጫ ታዛቢዎች ወደ ተለያዩ የሐሪቱ ክፍሎቸ ተንቀሳቀሱ ።

https://p.dw.com/p/NQJk
ምስል AP

ይኽው 60 አባላት ያሉት ቡድን በመላው የሐገሪቱ ክፍሎች 90 አባላት ያሉትን የህብረቱን የረዥም ጊዜ ቡድን እንደሚቀላቀል ህብረቱ አስታውቋል ። የታዛቢው ቡድን ሀላፊ ዛሬ አዲስ አበባ ውስጥ በሰጡት መግለጫ ፣ ለአጭር ጊዜ ምርጫውን የሚታዘበው ቡድን አባላት ፣ ከዚህ ቀደም በሐገሪቱ ምርጫ ለመታዘብ እንደተሰማሩት የህብረቱ ታዛቢዎች የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው እና ምርጫውንም በገለልተኝነት ለመታዘብ የሚያስችል ገለፃ የተሰጣቸው መሆኑን አስታውቀዋል ። ጋዜጣዊ መእግለጫውን የተከታተለው ታደሰ ዕንግዳው ዝርዝሩን ልኮልናል ።

ታደሰ ዕንግዳው ፣ ሂሩት መለሰ

ነጋሽ መሐመድ