1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ ላይ የጣለው ማዕቀብ

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2001

የአውሮፓ ህብረት በዚምባብዌ መንግስት ላይ የጣለውን ማዕቀብ ማጥበቁን ትናንት ባሳለፈው ውሳኔና ውሳኔውን በተከተለው መግለጫ አስታውቋል ።

https://p.dw.com/p/GhQz
ምስል AP

ትናንት ብረሰልስ ቤልጅየም የተሰበሰቡት የህብረቱ አባል ሀገራት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ከከዚህ ቀደሙ ጠንከር ያለ ተጨማሪ የማዕቀብ ውሳኔ ነው ያሳለፉት ። ህብረቱ ከአውሮፓ ኩባንያዎች ጋር ግንኙነት ያላቸው ተጨማሪ የዚምባብዌ ኩባንያዎች ንብረት እንዳይንቀሳቀስ የሚያግድና ከገዥው መንግስት ጋር የቅርብ ግንኙነት ያላቸው ተጨማሪ ሰዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ የሚጥል ውሳኔ አስተላልፏል ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ዝርዝሩን ልኮልናል ።