1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮፓ ህብረትና የቻይና ጉባኤ

ሐሙስ፣ መስከረም 27 2003

ትናንት ብራሰልስ ውስጥ የተካሄደው 13 ተኛው የአውሮፓ ህብረትና የቻይና ጉባኤ የጋራ ትብርን ለማጠናከር ና ወደፊት በጋራ ጉዳዮች ላይ የሚካሄደውን ውይይት ለመቀጠል በመስማማት ተጠናቋል ።

https://p.dw.com/p/PY7w
ዌን ዥባው በብራሰልስምስል AP

ሆኖም በሁለቱ ወገኖች የንግድ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ግንኙነቶች ላይ ያተኮረው ይኽው ጉባኤ የቻይናን የውጭ ምንዛሬ መርህ በመሳሰሉ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ ልዩነቱን ማጥበብ ሳይችል አብቅቷል ። በዚህ ጉባኤ ላይ የአውሮፓ ህብረትን ወክለው የአውሮፓ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሚስተር ሄርማን ቫን ሮምፖይ እና የህብረቱ ኮሚሽን ፕሬዝዳንት ሆሴ ማኑዌል ባሮሶ የተገኙ ሲሆን ቻይና ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትሯ በሚስተር ዌን ዥባው ነበር የተወከለችው ።

ገብያው ንጉሴ ፣ ሂሩት መለሰ

አርያም ተከሌ