የአውሮጳ ፖርላማ ልዑካን የኢትዮጵያ ጉብኝት
ሐሙስ፣ መጋቢት 29 2008ማስታወቂያ
በአውሮጳ ፓርላማ የሶሻሊስቶችና ዴሞክራቶች አባላት ቡድን ያዘጋጀው የአፍሪቃ ሳምንት መርሃ ግብር ካለፈው ማክሰኞ ጀምሮ ብራሰልስ ውስጥ በልዩ ልዩ ዝግጅቶች እየተካሄደ ነው። ይኽው ልዩ መርሃ ግብር ፣ ግጭቶችን በማስወገድ በሴቶችና በህጻናት መብቶች በትምህርትና በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ዝግጅቶችና ውይይቶች ተካሂደውበታል ። የዚህ መርሃ ግብር አዘጋጅ የአውሮጳ የሶሻሊስቶችና ዴሞክራቶች አባላት ቡድን ባለፈው ሳምንት አዲስ አበባ ውስጥ ከኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለ ማርያም ደሳለኝ ጋር ተነጋግሮ ነበር ። የብራሰልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሴ ስለ መርሃ ግብሩና ቡድኑ ከጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም ጋር ስላካሄደው ውይት ይዘት የቡድኑን ፕሬዝዳንት አነጋግሮ ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል ።
ገበያው ንጉሴ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ