1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ስምምነት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 6 2012

ቅዳሜ ዕለት በልዩ የተጠራው የብሪታንያ ምክር ቤት ጠቅላይ ሚንሥትሩ ያደረጉትን ስምምነት ይቀበላል አለያስ ውድቅ ያደርጋል ከነገ በስትያ የምናየው ይኾናል። የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዦን ክላውድ ዩንከር በትዊተር የማኅበራዊ ድረ-ገጻቸው የዛሬው ስምምነት በተመለከተ፦«ለብሪታንያም ኾነ ለአውሮጳ ኅብረት ፍትሓዊ እና ተመጣጣኝ ስምምነት ነው»

https://p.dw.com/p/3RTHB
Belgien Brüssel EU Gipfel | Barclay, Johnson, Juncker und Barnier
ምስል picture-alliance/PA Wire/S. Rousseau

የአውሮጳ ኅብረትና የብሪታንያ ስምምነት

ብሪታንያ ከአውሮጳ ኅብረት በምትወጣበት በ«ብሬግዚት» ውል ላይ ዛሬ ብራስልስ ውስጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል። የብሪታንያ ጠቅላይ ሚንሥትር ቦሪስ ጆንሰን ከአውሮጳ ኅብረት ጋር የደረሱትን ስምምነት ለሀገራቸውም ምክር ቤት ቅዳሜ ዕለት አቅርበው ማሳመን ነው የሚጠበቅባቸው። ቅዳሜ ዕለት በልዩ የተጠራው የብሪታንያ ምክር ቤት ጠቅላይ ሚንሥትሩ ያደረጉትን ስምምነት ይቀበላል አለያስ ውድቅ ያደርጋል ከነገ በስትያ የምናየው ይኾናል። የአውሮጳ ኅብረት ኮሚሽን ፕሬዚደንት ዦን ክላውድ ዩንከር በትዊተር የማኅበራዊ ድረ-ገጻቸው የዛሬው ስምምነት  በተመለከተ፦ «ለብሪታንያም ሆነ ለአውሮጳ ኅብረት ፍትሓዊ እና ተመጣጣኝ ስምምነት ነው» ሲሉ ጽፈዋል። ብሪታንያ እና የአውሮጳ ኅብረት የተስማሙበት ነጥብ ምን ይመስላል? ስምምነቱ ከተደረሰበት የቤልጂየሟ መዲና ብራስልስ ወኪላችን ገበያው ንጉሤ ጋር ስቱዲዮ ከመግባቴ በፊት ደውዬ ነበር። ገበያው የዛሬውን ስምምነት በማብራራት ይጀምራል። 

ገበያው ንጉሤ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ