1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጻ አፍሪቃ ንግድ ዉል ክሽፈት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 1 2000

በሊዝበን ፖርቱጋል ለጋራ ስልታዊ የንግድ ግንኙነት ከተሰበሰቡት የአፍሪቃ መንግስታት መሪዎች መካከል አንዳንዶቹ ዉሉን ከአዉሮጻዉ ህብረት ጋር መፈጸም ባለመፈለጋቸዉ ከህብረቱ ችግር ሊሚገጥማቸዉ እንደሚችል ተገለጸ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሪ የአዉሮጻዉ ህብረት አባል አገር የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉዳዩ ለመምከር በብረስል ስብሰባ ተቀምጠዋል

https://p.dw.com/p/E0a6
ፖርቱጋል የሊስበኑን ጉባኤ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ
ፖርቱጋል የሊስበኑን ጉባኤ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍምስል AP

ኦክስ ፋም ጀርመን የተሰኘዉ ግብረሰናይ ድርጅት የስምምነቱ ዉል እንደገና ሊጤን ይገባዋል ሲል ትናንት ባወጣዉ የጹሁፍ መግለጫ አሳስቧል።
በሊዝበን የተሰበሰቡት የአዉሮጻ ህብረት አባል አገሮች እና የአፍሪቃ መንግስታት መካከል ለሚደረገዉ የነጻ ንግድ ልዉዉጥ አዲስ የኢኮኖሚ ሽርክና ዉል ለማስፈን የተደረገዉ ጥረት የተሳካ አይመስልም። ለነጻ የንግድ ዉል የቀረበዉን የስምምነት ዉል በርካታ አፍሪቃ አገሮች ዉድቅ አድርገዉታል። በሊዝበን በተካሄደዉ ስብሰባ መጠናቀቅያ ላይ ሊፈጸም የታሰበዉ የስምምነት ፊርማ እስከ ያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ አመት መጨረሻ ድረስ ካልተጠናቀቀ ዉሉን ዉድቅ በሚያደርጉት አፍሪቃ አገራት ላይ የቀረጥ ጭማሪ ችግር ይደርሳል ሲል ህብረቱ አስጠንቅቆአል። በኦክስፋም ጀርመን በተሰኘዉ የግብረሰናይ ድርጅት ዉስጥ የንግድ ልዉዉጥ ምሁር የሆኑት ጀርመናዊትዋ Marita Wiggerthale እንደሚሉት በርግጥ ዉሉ ባልፈጸሙ የአፍሪቃ አገራት ላይ ችግር ይደርሳል ይላሉ
«ይህን ዉል ያልፈጸሙ የአፍሪቃ አገራት ምናልባትም የሚያቀርቡትን የምርት ዉጤት በዉጭ ገበያ ላይሸጡ ይችላሉ። በዚህም ምክንያት በአራቸዉ ዉስጥ የማምረቻ ኢንዱስትሪዎቻቸዉ የግብርና ተቋሞቻቸዉ ስራቸዉን ያቆማሉ፣ ያ ማለት ደግሞ፣ አምራቹ ግለሰብ የዛኑ ያክል ስራዉን ያቆማል። ለምሳሌ ይህንን ዉል አልፈርምም ካሉት መካከል በምዕራብ አፍሪቃ በትንሹ የ 1 ሚሊዮን ይሮ ቀዉስ ነዉ የሚደርስበት»


የአውሮፓ ሕብረት በአሕጽሮት ACP በመባል ከሚታወቀው የአፍሪቃ፣ የካራይብና የፓሲፊክ አካባቢ መንግሥታት ስብስብ ጋር አዲስ የኤኮኖሚ ሽርክና ውል ለማስፈን እንደ አዉሮጻዉያኑ የመጨረሻዉ ቀነ ቀጠሮ ለመድረስ ከዛሪ ጋር 20 ቀን ነዉ የቀረዉ። እስከያዝነዉ የአዉሮጻዉያኑ 2007 ዓ.ም. ማለት ነዉ። ግን ስኬት ማግኘቱ አጠራጣሪ ነዉ። አፍሪቃ የራስዋን ምርት በነጻ ገበያ ወደ አዉሮጻዉ ህብረት አገሮች ለማቅረብ የጋራ የንግድ ዉል ስምምነት አልፈጽም የሚሉ የአፍሪቃ አገሮች በርካታ ቢሆኑም ድርድሩን ለማከናወን አሁንም ከአውሮፓ ኮሚሢዮን በኩል አንዳንድ የማግባባት ጥረት በመደረግ ላይ ነዉ። በሌላ በኩል የአዉሮጻዉ ህብረት የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በጉዳዩ ለመምከር እና የጉዳዩን አስፈላጊነት ለማስገንዘብ ዛሪ ብረስልስ ላይ ተቀምጠዋል። ኦክስፋም ጀርመን የአዉሮጻዉ ህብረት ዉሉን በሌላ መልክ ማቅረብ አለበት ዉሉ በተለይ ለታዳጊዎቹ አገሮች አመች አይደለም ይላል።
«ኦክስፋም አዉሮጻዉ ህብረት የንግድ ዉል ስምምነቱን እንዲያጠናዉ ያሳስባል። የአፍሪቃ የካራይብና የፓሲፊክ አካባቢ መንግስታት የኢኮኖሚ ሽርክና ዉል በሚቀጥለዉ የአዉሮጻዉያኑ 2008 አ.ምህርም ቢሆንም የተስተካከለና ነጻ ንግድ ልዉዉጥ እንዲፈጸም ይላል። እንደ ኦክስፋም የአሁኑ የንግድ ዉል ስምምነት ለእሪቃዉያኑ አገራት በኢኮኖሚ፣ በንግድ እንዲሁም በምግብ አቅርቦት ላይ ትልቅ ጉዳት ያስከትላል»


ዉሉ ለታዳጊዎቹ አገሮች ልማት ከመበጀቱ ይልቅ የእስካሁኑን ስምምነት ህገወጥ ያደረገዉን የአለም ንግድ ድርጅትን የጊዜ ገደብ ለማክበር ተብሎ ከተፈጸመ ከመንግስት ነጻ የሆኑ ድርጅቶች እንደሚሉት ትክክለኛ አይደለም። ከታዳጊዉ አለም ስብስብ በርከት ያሉት የደሃ ድሃ የሚባሉት ሃገራት በፊናቸዉ ዉሉ እስካሁን ወደ አዉሮጻ ገባያ ለመዝለቅ ተሰጥቶአቸዉ የቆየዉን ልዩ የንግድ አስተያየት ከንቱ የሚያደርግ ከሆነ ለመፈረም ዝግጁ አለመሆናቸዉን በየግዜዉ ሲያዝገነዘቡ መቆየታቸዉ የሚታወስ ነዉ።