1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳ የእግር ኳስ ግጥምያና ፈረንሳይ

ዓርብ፣ ሰኔ 3 2008

ፈረንሳይ የምታስተናግደዉ የአዉሮጳ የእግር ኳእ ዋንጫ ሻንፕዮናያ ትናንት ምሽት ፓሪስ እንብርት ላይ በተዘጋጀ ይፋዊ የመክፈቻ ሥነ-ስርአት ከፍተኛ የሙዚቃ ድግስ ተካሂዶአል።

https://p.dw.com/p/1J4cE
Frankreich Paris Fans mit Fähnchen
ምስል picture-alliance/dpa/A. Morissard

ፓሪስ ከተማ ባለፈዉ ኅዳር ወር ላይ በአሸባሪ ጥቃት ከደረሰባት በኋላ ዛሬ የዓለም የእግር ኳስ አፍቃሪም ሆነ የብዙኃን መገናኛዎች ዓይናቸዉን ወደ ፓሪስ መልሰዋል። ፓሪስ ላይ የሚጀምረዉ የዘንድሮዉ ግጥምያ አዘጋጅዋ ፈረንሳይና ሮማንያ ይጋጠማሉ። እንደሚታወቀዉ ባለፈዉ ኅዳር ወር ፓሪስ ላይ በአሸባሪዎች ከፍተኛ ጥቃት፤ ከ100 በላይ ሰዎች ተገድለዋል። ከዚህ ሌላ ፓሪስ የስራ ማቆም አድማ፤ እንዲሁም ሌሎች በርካታ ማኅበራዊ ችግሮችን ተጋፍጣ ነዉ የሰነበተችዉ። ፈረንሳይ የአዉሮጳ የእግር ኳስ ዋንጫ ግጥምያን ስታስተናግድ ያሉባትን ችግሮች ቀርፋ ይሆን? የደሕንነቱ ጥበቃስ ምን ይመስላል? ፓሪስ ፈረንሳይ የምትገኘዉ ወኪላችንን በስልክ ጠይቀናታል።


ሃይማኖት ጥሩነህ


አዜብ ታደሰ

ኂሩት መለሰ