1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአዉሮጳዉያኑ 2010ዓ,ምና የተፈጥሮ ክስተት

ማክሰኞ፣ ታኅሣሥ 19 2003

በአዉሮጳዉያኑ 2010ዓ,ም በተፈጥሮ እና በሰዉ ሠራሽ ምክንያት የደረሱ አደጋዎች በገንዘብ ሲመነዘሩ 222 ቢሊዮን ዶላር እንዳከሰሩ ይፋ ሆኗል።

https://p.dw.com/p/QkkD
የመሬት መንቀጥቀጥ ያንኮታኮታት ሄይቲምስል AP

ይህም አምና በ2009ዓ,ም ከደረሰዉ ኪሳራ የ63ቢሊዮን ጭማሪ አመልክቷል። ከአዉሮጳዉያኑ 1976ዓ,ም ወዲህም በዓለም ዙሪያ በተከሰቱ የተፈጥሮ አደጋዎች በተሰናባቹ የአዉሮጳዉያን ዓመት 2010 በሰዎች ህይወት ላይ የደረሰዉ ጥፋት እጅግ ከፍተኛ መሆኑ ተገልጿል። ዘንድሮ 260,000 ሰዎች በያለበት በረሱ አደጋቸዉ ህይወታቸዉን አጥተዋል። በያለበት በደረሰዉ አደጋ ከጠፋዉ የሰዉ ህይወት የሄይቲዉ የመሬት መንቀጥቀጥ ከፍተኛዉን የሰዉ ልጅ ህይወት አስገብሯል። 222,000።

ሸዋዬ ለገሠ

አዜብ ታደሰ