1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪው ኢትዮጵያዊ ጥረትና ዉጤት

ማክሰኞ፣ ሐምሌ 18 2009

የድሬዳዋዉ ነዋሪ አቶ በያን መለስ የተፍጥሮ አደጋን በተፈጥሮ ዛፍ ለመመከት መጣር ከጀመሩ ዘንድሮ አስራ-አንደኛ አመታቸዉን ይዘዋል። በ1998 ድሬዳዋን ባጥለቀለቀዉ ጎርፍ ሰባት የቤተሰብ አባሎቻቸዉን ያጡት አቶ በያን ተመሳሳይ አደጋ እንዳይደረስ እንደመከላከያ ያዩት ጎርፍ የሚያልፍበትን አካባቢ በዛፍ ማልበስ ነዉ።

https://p.dw.com/p/2h7zq
Äthiopien Dire Dawa - Beyan Tessema Pflanzt Bäume nach Flut
ምስል DW/Y. Gebregziabher

የአካባቢ ጥበቃ ተቆርቋሪው ኢትዮጵያዊ ጥረትና ዉጤት

የተከሏቸዉ ችግኞች ዛሬ አድገዉ የቁሻሻ መጣያ የነበረዉን አሸዋማ አካባቢ ወደ ደንነት ቀይረዉታል። ወደ ድሬዳዋ የተጓዘዉ ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር የአቶ በያንን ጥረትና ዉጤት በዛሬዉ ጤናና አካባቢ ዝግጅታችን ባጭሩ ይቃኛል።

 

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር

ነጋሽ መሀመድ