1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ዘገባና የዓለም አስተያየት

ሐሙስ፣ ጥቅምት 30 2004

ዓለም ዓቀፉ የአቶም ኃይል ተቆጣጣሪ ድርጅት በእንግሊዘኛው ምህፃር IAEA ከትናንት በስተያ ስለ ኢራን የአቶም ኃይል መርሃ ግብር ያቀረበው አዲስ ዘገባ ላይ ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ የተለያዩ አስተያየቶችን እየሰጠ ነው ።

https://p.dw.com/p/RvoV
የኢራን ኒዩክልየር ማብላያምስል picture alliance/dpa

ዩናይትድ ስቴትስ ዘገባውን አስደንጋጭ ስትለው ኢራን ደግሞ ሃሰት ስትል አጣጥላዋለች ። ጀርመን ብሪታኒያ እና ፈረንሳይ በቴህራን መንግሥት ላይ ጥብቅ ማዕቀቦች እንዲጣሉ ጥሪ ሲያቀርቡ ሩስያ ደግሞ አዲስ ማዕቀብን ተቃውማለች ። ቻይናም ማዕቀብ መፍትሄ አይሆንም ብላለች ። እስራኤል በበኩሏ ዓለም ዓቀፉ ማህብረሰብ አንድ እርምጃ እንዲወስድ አሳስባለች ።

ሂሩት መለሰ

አርያም ተክሌ