1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአትሌት ዝናሽ ገዳይ

ዓርብ፣ ኅዳር 22 2010

የአትሌቷን አሟሟት ለሚያጣራው አካል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የ28 ዓመቱ ተጠርጣሪ አትሌት ዝናሽን በትራስ እንዳፈናት እና መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ከነበሩት የተለያዩ ዋንጫዎች በአንዱ እንደመታት አምኗል።

https://p.dw.com/p/2ocb6
Symbolbild Kerze Flamme
ምስል Colourbox

የአትሌት ዝናሽ ገዳይ እጁን ሰጠ  

የ27 ዓመትዋን ኢትዮጵያዊት አትሌት ዝናሽ ገዝሙን ከፓሪስ ወጣ ብሎ በሚገኝ አካባቢ በመግደል የተጠረጠረው ኢትዮጵያዊ ትናንት ለፖሊስ እጁን መስጠቱን የፈረንሳይ ፖሊስ አስታወቀ። የአትሌቷን አሟሟት ለሚያጣራው አካል ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለፈረንሳይ ዜና አገልግሎት እንደተናገሩት የ28 ዓመቱ ተጠርጣሪ አትሌት ዝናሽን በትራስ እንዳፈናት እና መኖሪያ ቤቷ ውስጥ ከነበሩት የተለያዩ ዋንጫዎች በአንዱ እንደመታት አምኗል። የማራቶን ሯጭ የአትሌት ዝናሽ አስከሬን በዚህ ሳምንት ማክሰኞ በጥቆማ መገኘቱን ከፓሪስ ወጣ ብላ የምትገኘው የቦቢኚ አቃቤ ሕግ አስታውቋል። አትሌት ዝናሽ «ስታድ ፍሮንሴ» በተባለው የአትሌቲክስ ክለብ ውስጥ በቅርቡ መግባቷ ተዘግቧል። ባለፈው ዓመቱ የአምስተርዳም የማራቶን ውድድር ተሳትፋም ውድድሩን በሁለት ሰዓት ከ32 ደቂቃ መጨረሷ ተነግሯል። አትሌቷን በመግደል የተጠረጠረው ማንነቱ ያልተገለፀው ኢትዮጵያዊ በማራቶን ውድድር ለመካፈል ከሁለት ዓመት በፊት ፈረንሳይ መምጣቱም ተጠቅሷል። ዝርዝሩን የፓሪስዋ ዘጋቢያችን ሃይማኖት ጥሩነህ ልካልናለች።   
ሃይማኖት ጥሩነህ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ