1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአብዪይ የሱዳን የነዳጅ አካባቢ ዉጥረት

ሰኞ፣ ግንቦት 15 2003

ደቡብ ሱዳን ከሰሜን ሱዳን ክፍል በመገንጠል ነጻነትዋን በይፋ ልታዉጅ ጥቂት ሳምንታት ሲቀራት፣ በነዳጅ ዘይት ሃብት በታደለችዉ የአብዪይ አካባቢ የባለቤትነት ጉዳይ ሌላ አዲስ ጦርነት እንዳይቀሰቅስ አስግቶአል።

https://p.dw.com/p/RPL9
ምስል DW


የሰሜን ሱዳን ጦር በራሱ መግለጫ መሰረት የአብዪይን ግዛት በቁጥጥሩ እንዳደረገ ገልጾአል። የካርቱም መንግስታዊ ቴሌቭዥን እንደዘገበዉ የሰሜን ሱዳን ጦር የጠላት ሃይል ያላቸዉን ተዋጊዎች ከአብዪይ አስወጥቶአል። ግጭቱ የጀመረዉ ባለፈዉ ሃሙስ የሰሜን ሱዳን ጦር ወታደሮቹ በደቡቡ ክፍል ሃይል ተጠቅተዉ መገደላቸዉን ካስታወቀ በዃላ ነበር። የደቡብ ሱዳን ህዝብ ባለፈዉ ጥር ወር ተካሂዶ በነበረዉ ህዝበ ዉሳኔ በሰፊ ድምጽ ነጻነትን መምረጡን ማሳየቱ አይዘነጋም። በነዳጅ ዘይት ሃብት የታደለችዉ የአብዪይ አካባቢ እጣ ፈንታ ግን መፍትሄ ሳያገኝ አጨቃጫቂ ሆኖ ቀጥሎአል።


አዜብ ታደሰ
መስፍን መኮንን