1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

አባባ ተስፋዬ

ረቡዕ፣ ሐምሌ 26 2009

በ96 ዓመታቸው ከትናንት በስቲያ ያረፉት አባባ ተስፋዬ ዝነኛ ተዋናይ ድምጻዊ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች የውዝዋዜ አሰልጣኝ ደራሲ እና የምትሀት ባለሞያም ነበሩ።

https://p.dw.com/p/2hacf
Äthiopien Beerdigung des Künstlers Tesfaye Sahlu
ምስል DW/G. Tedla

የአባባ ተስፋዬ የቀብር ሥርዓት

 
የተወዳጁ አርቲስት የተስፋዬ ሳህሉ የ(አባባ ተስፋዬ) የቀብር ስርዓት ዛሬ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ተፈፀመ።  ለ42 ዓመታት ያለማቋረጥ  ተረት ሲያቀርቡ በቆዩበት በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልጆች ክፍለ ጊዜ ይበልጡን የሚታወቁት አበባ ተስፋዬ ለልጆች በሚለግሱት ምክርም ይወደዳሉ። በ96 ዓመታቸው ከትናንት በስቲያ ያረፉት አባባ ተስፋዬ ዝነኛ ተዋናይ ድምጻዊ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋች የውዝዋዜ አሰልጣኝ ደራሲ እና የምትሀት ባለሞያም ነበሩ። ዶይቼቬለ በአርቲስቱ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ ያነጋገራቸው አንድ የሙያ ባልደረባቸው አባባ ተስፋዬ ኮሜድያን እንደነበሩም አስታውሰዋል። በቀብሩ ላይ የተገኘው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ አለው።
ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ
ኂሩት መለሰ
አርያም ተክሌ