1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የአሸንዳ ወይም የሻደይ በአል አከባበር

ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2002

ሃይማኖታዊ መነሻ እንዳለዉ የሚነገርለት የሻደይ ወይም የአሸንዳ በአል በሰሜን ኢትዮጽያ አካባቢዎች እንዲሁም በኤርትራ በደማቅ ሁኔታ ይከበራል።

https://p.dw.com/p/P2PU
ምስል DW

የሴትች በተለይም የልጃገረዶች በአል መሆኑም ይነገርለታል። የሻደይ በአል በተለይ በወሎ አካባቢ በደመቀ እደሚከበር፣ ሴቶች በዚህ በአል ወቅት አምረዉ እና ተዉበዉ ከቤታቸዉ የሚወጡበት የሚታጩበት በሌላ በኩል በአካባቢዉ ባለ ማህበረስ የተጣላ የሚታረቅበት፣ ሰፋ ያለ ገበያ የሚደራበት እንደሆነ በደሴ ዪንቨርስቲ መምህርት ጸዳለ ተፈራ ይገልጻሉ፣ በመቀሌ ዪንቨርስቲ የቋንቋ ምሁር አቶ ትካቦ ገብረስላሴ በአካባቢያቸዉ አሸንዳ እጅግ በጉጉት የሚጠበቅ የሴቶች በአል እንደሆነ እና እስከ ዘመን መለወጫ እየተከበረ የሚቆይ መሆኑን ይናገራሉ።


አዜብ ታደሰ

ሸዋዪ ለገሰ